Quantcast
Channel: ኢታኖል
Viewing all 339 articles
Browse latest View live

የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በባህር ዳር ተካሄደ

$
0
0

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሊያከናውናቸው ካቀዳቸው ዓመታዊ የአገር ውስጥ ውድድሮች የግማሽ ማራቶን ውድድር እሑድ ኅዳር 25 ቀን 2009 ዓ.ም. በባህር ዳር ከተማ አካሂዷል፡፡

በውድድሩ የተለያዩ ታዋቂና አዳዲስ አትሌቶች ተሳታፊ መሆን የቻሉ ሲሆን፣ አትሌቶቹም ኢትዮጵያን ወክለው በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ለመሳተፍ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ የአገር ውስጥ ውድድሮች ራሳቸውን የበለጠ ለመገምገም እንደሚያግዛቸውም ተናግረዋል፡፡

በአሥረኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ላይ በመሳተፍ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ታምራት ቶላ፣ በአገር ውስጥ የሚዘጋጁ እንደነዚህ መሰል የተለያዩ ውድድሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚደረጉት ፉክክሮች የተሻለ እገዛ እንደሚያደርጉ ነው ያስረዳው፡፡

እንደ አትሌቱ አስተያየት ከሆነ፣ አገሪቱ በዓለም መድረክ ላይ የነበራትን የአትሌቲክስ ታሪክ ከቀድሞ በተሻለ ለመሥራት የአገር ውስጥ ውድድሮችን ቁጥር በመጨመር፣ ቀደም ብሎ ማጠናቀቅ እንደሚያስፈልግም ተናግሯል፡፡

በሪዮው 31ኛው የሪዮ ኦሊምፒያድ የአሥር ሺሕ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት የነበረው ታምራት በአገር ውስጥ የሚደረጉት ውድድሮች ውስንነትና የአትሌቶች በቡድን አለመሥራት ለአትሌቲክሱ ውጤት ማሽቆልቆል ምክንያት እንደሆነ ገልጿል፡፡

በ2008 ዓ.ም. በሰበታ ከተማ በተካሄደው ዘጠነኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው አትሌቱና በእንግሊዝ ካርዲፍ ሲቲ በተዘጋጀው ግማሽ ማራቶን መሳተፉ ይታወሳል፡፡ በውድድሩ ርቀቱን በአንድ ሰዓት 00፡06 ሰከንድ በማጠናቀቅ አምስተኛ ደረጃ ይዞ መጨረሱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱም የኬንያውያን የቡድን ሥራ ጠንካራ መሆን የበላይነቱ ሊወሰድበት እንደቻለ ሁኔታውን በቁጭት ያስታውሳል፡፡ በሪዮ ኦሊምፒክ በ10 ሺሕ ሜትር ላይ በቴክኒክ ጉዳይ በእንግሊዛዊ ሞ ፋራ ብልጫ የተወሰደበት እንዳስቆጨውም አልሸሸገም፡፡

ኢትዮጵያ በረዥም ርቀት ያላትን ታሪክ በነበረበት ለማስቀጠልና ከተፎካካሪዋ ኬንያ ጋር በዓለም አቀፍ መድረክ የተሻለ ሆና ለመቅረብ ሁሉም አትሌቶች የውድድር ዕድል ተፈጥሮላቸው በአገር ውስጥ የቡድን ስሜቱን መፍጠር ዋነኛው የቤት ሥራ እንደሆነ አትሌቱ ይናገራል፡፡

በረዥም ርቀት ጠንክሮ እንደሚሠራ የሚናገረው አትሌቱ በ10,000 እና ግማሽ ማራቶን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ጠንካራ ሆኖ መቅረብ ዕቅዱ እንደሆነም አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

በ10ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ኦሮሚያ ፖሊስን በመወከል 1 ሰዓት ከ01 ደቂቃ ከ53 ያጠናቀቀው ታምራት፣ በሪዮ ኦሊምፒክ ላይ የተገኘውን የ10,000 ሜትር ውጤት ዘንድሮ በለንደን በሚደረገው የዓለም ሻምፒዮና ላይ አሸናፊ ለመሆን ከወዲህ ጠንክሮ እየሠራ እንደሚገኝ ጭምር አብራርቷል፡፡

በ20ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑን የአመራር ኃላፊነት የተረከቡት የቀድሞ አንጋፋ አትሌቶች መመረጥ በተመለከተ፣ አትሌቲክሱ ወደ ተሻለ ደረጃ ማደግ ይችል ዘንድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም አልሸሸገም፡፡

‹‹ፌዴሬሽኑ በአትሌቶች መመራቱ አትሌቶች ምን ዓይነት ሥልጠና ማድረግ እንዳለባቸው፣ የሚያጋጥማቸውን ችግር እንዴት መፍታት እንደሚችሉና ውድድሮቻቸውን እንዴት ማከናወን እንዳለባቸው በቅርበት ስለሚያውቁት ለመነጋገር ጭምር ይረዳል›› በማለት አትሌቱ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በቅርበት መጥቶ ስላለው ወቅታዊ የአትሌቲክስ ጉዳይ እያማከረው እንደሆነም ሳይገልጽ አላለፈም፡፡

አትሌቶች ስለሚያደርጉት ልምምድ ያብራራው አትሌቱ፣ ‹‹ውድድር ሳይሆን ልምምድ ማድረግ ከባድ ነው፣ በማለት ልዩነቱን የገለጸ ሲሆን፣ በአንፃሩ በልምምድ ወቅት የአትሌቶችን አቅምና ፅናት ለይቶ ለማወቅ የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው ጭምር ተናግሯል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አትሌቶችን ከክልል በማምጣትና ፉክክርን በማስፋት በቀጣይ ለሚደረጉ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ጠንክሮ መሠራት ያስፈልጋልም ብሏል፡፡

በአሥረኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በስተቀር ስምንት ክልሎችና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ 13 ክለቦችና በግል የቀረቡ 79 ሴቶችና 154 ወንዶች በድምሩ 233 አትሌቶች ተሳትፈውበታል፡፡

በሴቶች ታደለች በቀለ ከኦሮሚያ ማረሚያ ርቀቱን 1 ሰዓት፣ 10 ደቂቃ፣ 28 ሰከንድ በሆነ ጊዜ አጠናቃ አሸናፊ ሆናለች፡፡ እሸቴ በከሪ ከኦሮሚያ ፖሊስ 1 ሰዓት፣ 11 ደቂቃ፣ 13 ሰከንድ ሁለተኛ፣ ጉሉሜ ቶሎሳ ከኦሮሚያ ፖሊስ ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

በወንዶች ታምራትን ተከትለው የገቡት ጌታነህ ጫላ መከላከያ 1 ሰዓት፣ 02 ደቂቃ፣ 28 ሰከንድ ሁለተኛና አረዶም ጥዑማይ ከመሰቦ ሲሚንቶ 1 ሰዓት፣ 02 ደቂቃ 40 ሰከንድ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

በሻምፒዮናው አሸናፊ ለሆኑት በሁለቱም ጾታ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ለወጡ አትሌቶች የሜዳሊያ ሽልማት የተሰጠ ሲሆን፣ በተጨማሪም በግል ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ለወጡ አትሌቶች ከ20 ሺሕ እስከ ሦስት ሺሕ ብር ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት ተሸልመዋል፡፡ 

Standard (Image)

አምስተኛዋ ኢትዮጵያዊት የዓለም ኮከብ

$
0
0

በብራዚል አስተናጋጅነት ባለፈው ክረምት በተከናወነው 31ኛው ኦሊምፒያድ ለኢትዮጵያ ብቸኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበችው አልማዝ አያና የዓለም ኮከብ አትሌት ሆና ተመርጣለች፡፡ በወንዶች በአጭር ርቀት የዓለም ፈጣኑ አትሌት ጃማይካዊው ዩዜን ቦልት ክብሩን አግኝቷል፡፡

የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) በሞናኮ ባለፈው ዓርብ እ.ኤ.አ. ለ2016 የውድድር ዓመት ለኮከብ አትሌት ምርጫ በሴቶች ካቀረባቸው መካከል አልማዝ አያና አሸናፊ ሆናለች፡፡ አትሌቷ ለዚህ ክብር የበቃችው ከጃማይካዊቷ የአጭር ርቀት ተወዳዳሪ ኤሳኔ ቶምፕሰንና ከፖላንዳዊቷ የመዶሻ ወርዋሪዋ አኔታ ቮድርቼክ ልቃ በመገኘቷ መሆኑ የአይኤኤኤፍ ዘገባ አስመልክቷል፡፡ አልማዝ በሪዮ ኦሊምፒክ የ10,000 ሜትር አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ከማስመዝገቧ በተጨማሪ በ5,000 የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት መሆኗ ይታወሳል፡፡

ከአዲስ አበባ 657 ኪሎ ሜትር ርቃ ከምትገኘው ቤንሻንጉል ጉሙዝ የተገኘችው አልማዝ አያና፣ በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ መድረኮች በውድድር ዓመቱ ሮም ላይ በተደረገው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በ5,000 ሜትር የአሸናፊነቱን ድል ስትቀዳጅ፣ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 14 ደቂቃ 12 59 ሰከንድ የወሰደባት ጊዜ የዓመቱ ምርጥ ሁለተኛ ሰዓት ነበር፡፡ አትሌቷ በሞናኮ በተከናወነው ሥነ ሥርዓት የተቀዳጀችው ክብር ከኢትዮጵያውያቱ እንስቶች ሦስተኛዋ እንድትሆን አስችሏታል፡፡ ከዚህ በፊት መሠረት ደፋርና ገንዘቤ ዲባባ የክብሩ ባለቤት መሆናቸው ይታወሳል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2010 በካናዳ በተዘጋጀው የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና የመጀመሪያዋን ዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ አንድ ብላ እንደጀመረች የሚነገርላት አልማዝ በወቅቱ በ3,000 ሜትር ተወዳድራ ርቀቱን 9 ደቂቃ 08 08 ሰከንድ አጠናቃ አምስተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቋ ግለ ታሪኳ ያስረዳል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም በዚሁ ርቀት ስትወዳደር መቆየቷ ይነገራል፡፡

በመካከለኛው ርቀት ብዙም መጓዝ ያልቻለችው አልማዝ እ.ኤ.አ. ከ2014 በሞሮኮ ማራካሽ በተከናወነው የአፍሪካ ሻምፒዮና በ5,000 ሜትር ተወዳድራ የርቀቱ አሸናፊም ለመሆን በቅታለች፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ በቻይና ቤጂንግ በተዘጋጀው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ5,000 ሜትር አገሯን ወክላ የቀረበችው አልማዝ የአይበገሬነቷ ሚስጥር ጎልቶ መውጣት ጀመረ፡፡ በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የቆየው የርቀቱን ክብረወሰን በሁለት ደቂቃ በማሻሻል በእጇ ማስገባት የቻለችበትን ጊዜ ማስመዝገቧም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ባለፈው ክረምት በተከናወነው የሪዮ ኦሊምፒክ በ10,000 ሜትር ያስመዘገበችው አዲሱ የዓለም ክብረ ወሰንም ለ23 ዓመታት ተይዞ የቆየ መሆኑ  አይዘነጋም፡፡

አልማዝ አያና ይህንን ክብር ካገኙ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አምስተኛዋ ስትሆን፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን በቅርቡ ወደ ኃላፊነት የመጣው ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴና ቀነኒሳ በቀለ መሸለማቸው ይታወሳል፡፡

 

 

Standard (Image)

የቴኳንዶ አሶሴሽን ወደ ብሔራዊ ፌዴሬሽን አደገ

$
0
0

የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ አሶሴሽን ወደ ፌዴሬሽን ማደጉን ተከትሎ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱ ተገለጸ፡፡

ቀድሞ በፌዴራል ደረጃ ተቀምጦ የነበረውና በማስተር ኪሮስ ገብረመስቀል ሲመራ የቆየው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ አሶሴሽን፣ ከ36 በላይ ሕጋዊ የሆኑ ውድድሮች ላይ ይሳተፉ የነበሩ ክለቦች ያሉት ማኅበር በመሆኑ፣ ወደ ፌዴሬሽን ደረጃ በማደግ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን መሆን ችሏል፡፡

ሐሙስ ኅዳር 29 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ስር ሲመራ የነበረው የአዲስ አበባ ቴኳንዶ አሶሴሽን በፌዴሬሽን ደረጃ መቀመጥ መቻሉን አሳውቋል፡፡

በዚህም መሠረት ከክልል የሶማሌና አማራ ክልሎችን ተከትሎ በፌዴሬሽኑ ስር ለመተዳደር ፈቃደኝነቱን የገለጸው የአዲስ አበባ ቴኳንዶ አሶሴሽን መጠሪያውን በመቀየር የአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን በሚል እንደሚጠራ ተገልጿል፡፡ በዕለቱ በተደረገው የማስተዋወቅ ሥነ ሥርዓት ላይም የመተዳደሪያና የመቋቋሚያ ደንበ የፀደቀ ሲሆን፣ የጽሕፈት ቤት ኃላፊና ፕሬዚዳንት ምርጫ አከናውኗል፡፡

ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ የተለያዩ የቴኳንዶ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በአሶሴሽን ደረጃ ሲያከናውን የቆየው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ፈቃድን ለማግኘት ጥያቄውን ከሁለት ዓመት በፊት አቅርቦ በ2009 ዓ.ም. መጀመሪያ ወር ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ተቀባይነት ማግኘቱን ፕሬዚዳንቱ ማስተር ኪሮስ ገብረመስቀል ለሪፖርተር አብራርተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከ45 ክለቦች በላይ፣ በኦሮሚያ 75 ክለቦች እንዲሁም በተመሳሳይ ሁኔታ በአማራ፣ ትግራይና ደቡብ ክልሎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ክለቦች መኖራቸውን ተጠቁሟል፡፡

በማኅበር ስር ሆኖ የተለያዩ ውድድሮችና ሥልጠናዎችን ሲያከናውን የነበረው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን፣ ‹‹ከአምስት ክልሎች በላይ ስፖርቱን በማስፋፋቱና የተለያዩ ውድድሮችን በማድረግ ወደ ፌዴሬሽን ማደግ ችሏል›› በማለት ፕሬዚዳንቱ አብራርተዋል፡፡ በፌዴሬሽን ደረጃ መቀመጡ የራሱ ሥራ አስፈጻሚ ተመድቦለት፣ ዓመታዊ በጀት ተወስኖለትና የውድድር ቁጥር በመጨመር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪዎችን ማፍራት እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በፌዴሬሽን ስር መሆኑ ዓለም አቀፍ ግንኙነትን ከማጠናከር አንፃር ከቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍን ለማግኘት ጠቀሜታ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

የባለሙያ እጥረትን በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ የጥራት ችግር ካልሆነ በስተቀር እምብዛም እንደ ችግር የሚነሳ ጉዳይ እንዳልሆነ ማስተር ኪሮስ አብራርተዋል፡፡

በአሶሴሽን ደረጃ ተዋቅሮ እንቅስቃሴውን ከጀመረ 11 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን፣ ሦስት ኢንተርናሽናል ውድድሮች ላይ መሳተፍ ሲችል በኢትዮጵያ ደግሞ አንድ የአፍሪካ ሻምፒዮን ማዘጋጀት ችሏል፡፡

በሻምፒዮናው ላይም የህንድ፣ አሜሪካና እንግሊዝ በተጋባዥነት ተገኝተው ከመሳተፋቸው ባሻገር የቁሳቁስ ድጋፍ ማበርከት መቻላቸው ጭምር ተጠቁሟል፡፡

Standard (Image)

ዳይመንድ ሊግ የሽልማት መጠኑን ከፍ አደረገ

$
0
0

ዓመታዊ የዳይመንድ ሊግ የአትሌቲክስ ውድድር ለአሸናፊዎች የሚሰጠውን የሽልማት መጠን ከፍ ማድረጉን የውድድር አዘጋጁ በድረ ገጹ አስታውቋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2017 ለሚደረጉት ዓለም አቀፍ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች 3.2 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን መረጃው ያመለክታል፡፡

በቀጣይ ለማከናወን ከታቀዱት ውድድሮች ተወዳዳሪዎች በሚያገኙት ነጥብ የሚመዘኑ ሲሆን፣ በመጀመሪያ የአይኤኤፍ ዳይመንድ ሊግ በ32 የውድድር ዓይነቶች ለሚወዳደሩና ውጤታማ ለሚሆኑ 100,000 ዶላር፣ ሁለት የፍጻሜ ውድድር ላይ ለሚያሸንፉ 50 ሺሕ ዶላር ተዘጋጅቷል፡፡

በውድድሩ ላይ የሚያሳዩት ብቃት ከግምት ውስጥ በማስገባትም ተጨማሪ ጉርሻ እንደተዘጋጀ ተገልጿል፡፡ እንደ ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማኅበር አይኤኤኤፍ ፕሬዚዳንት ሰባስትያንኮ አስተያየት ከሆነ፣ ‹‹ምንም እንኳ የዳይመንድ ሊግን ውድድር ከጀመረ ሰባት ዓመት ብቻ ቢሆንም የሽልማት ክፍያን ከፍ በማድረግ በቀጣይ ውድድሩ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ መንገድ ይከፍታል፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡

በ32 የውድድር ዓይነቶች ላይ አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች ከ50 ሺሕ እስከ 2000 ዶላር ድረስ እንደየደረጃቸው መሸለም እንደሚችሉ በድረ ገጹ ተቀምጧል፡፡ በሜዳ ተግባር ውድድር ላይ ለሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ ቀደም ሦስት የሙከራ ጊዜ የሚሰጣቸው የነበረ ሲሆን፣ በዘንድሮ ውድድር ግን ምርጥ አራቶች ብቻ ሦስት የድጋሚ ሙከራ እንደሚሰጣቸው ተጠቁሟል፡፡

የአይኤኤኤፍ ዳይመንድ ሊግ ዓመታዊ የአትሌቲክስ ውድድር ሲሆን፣ አትሌቶች በግላቸው በመሳተፍ ከፍተኛ ገንዘብ የሚሰበስቡበት ውድድር ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ2010 የጀመረው የውድድር መርሐ ግብር በአውሮፓ፣ እስያ፣ ሰሜን አሜሪካና አፍሪካ ላይ ይካሄዳል፡፡

በ2017 የውድድር ፕሮግራምም 14 የዳይመንድ ሊግ ሻምፒዮናዎች በተለያዩ የዓለም አገሮች ለማከናወን ታቅዷል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ገንዘቤ ዲባባ፣ አልማዝ አያና፣ ታምራት ቶላ፣ ሐጎስ ገብረሕይወትን ጨምሮ በርካታ አትሌቶች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እንደ 2015 የዳይመንድ ሊግ የክፍያ መረጃ መሠረት ከኢትዮጵያ አትሌቶች በዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ተሳትፎ ከፍተኛ ተከፋይ በመሆን 14ኛ ደረጃን በመያዝ ገንዘቤ ዲባባ ቀዳሚ ነች፡፡ 

Standard (Image)

ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ የቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

$
0
0

- የተወዳዳሪዎች የዜግነት ጉዳይ አከራክሯል

የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ሐሙስ ኅዳር 29 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባደረገው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስን የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡ የቅርጫት ኳስ ቀደምት ከሚባሉት ስፖርቶች አንዱ እንደመሆኑ የምሥረታ ዕድሜውን የሚመጥን ዕድገት ቀርቶ የነበረውን እንኳ ማስቀጠል እንዳልቻለ የሚናገሩ አሉ፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሐሙስ ኅዳር 29 ቀን የጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ከወራት በፊት ተደርጎ በነበረው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ፌዴሬሽኑን ለሦስት የኦሊምፒክ ዘመን በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠው በነበሩት አቶ ብርሃነ ከዳነማርያም ምትክ ምርጫ ለማድረግ ነበር፡፡ አቶ ብርሃነ በአሁኑ ወቅት የአምባሳደርነት ሹመት አግኝተው ከኢትዮጵያ ውጭ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፈዴሬሽን ያከናወነውን የምርጫ ሒደት አስመልክቶ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይመር ኃይሌ እንደሚናገሩት ከሆነ፣ ቀደም ሲል በተመረጡት ፕሬዚዳንት ምትክ አዲስ ምርጫ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት ስፖርቱን ሊያግዙ የሚችሉ ሰዎችን ወደ አመራር ለማምጣት በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ታምኖበት ነው፡፡ ለዚህ ማብራሪያቸው መነሻ ያደረጉት ዋና ጸሐፊ፣ በምርጫ አካሄድ ለአንድ የምርጫ ዘመን አንድ ጊዜ ምርጫ ከተደረገ በኋላና በሥራ ምክንያትም ሆነ በሌላ የተጓደሉ አመራሮች ቢያጋጥሙ ካሉት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ማሸጋሸግ ማስቀጠል ይቻላል የሚለው አሠራር እንዳለም አልሸሸጉም፡፡

በዚሁ መሠረት ክልሎችና ክለቦች እንዲያውቁት ተደርጎ ሦስት ዕጩ ተወዳዳሪዎች ማለትም ወ/ሮ ሚሚ ስብሐቱ ፌዴሬሽኑ የተወዳዳሪዎችን ግለ ታሪክ ሲያቀርብ ስማቸው እጅጋየሁ ስብሐቱ ብሎ ነው ያቀረበው፣ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስና የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ደምመላሽ ገብረሚካኤል እንደነበሩ የሚናገሩት የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ ጉባኤው በሰጠው ድምፅ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል ብለዋል፡፡

ከምርጫው አስቀድሞ ከወ/ሮ ሚሚ ስብሐቱ ውክልና ጋር ተያይዞ ‹‹ኢትዮጵያዊት አይደሉም›› በሚል አንዳንድ የጉባኤው ተሳታፊዎች ጥያቄ ተነስቶ ነበር፡፡ ለጥያቄው ማብራሪያ የሰጡት አቶ ይመር፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሚመራው በማኅበራት ማደራጃ መመርያ መሠረት እንደሆነና በመመርያውም ማንኛውም ሰው ለመመምረጥም ሆነ ለመመረጥ ‹‹ኢትዮጵያዊ መሆን እንዳለበት›› እንደሚል አብራርተው፣ ወ/ሮ ሚሚ ስብሐቱን የወከላቸው ክልል [የትግራይ ክልል] ይህንን ጉዳይ አጣርቶ መላክ እንደነበረበት ነው ያስረዱት፡፡ የፌዴሬሽኑ ድርሻ ክልሎች ተወካዮቻቸውን የሚያሳውቁበትን ቅጽ በቀኑና በወቅቱ ማድረስ ካልሆነ ጉዳዩ ከክልሉ አልፎ ፌዴሬሽኑን እንደማይመለከት ጭምር ተናግረዋል፡፡

ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽንን ጨምሮ የአንዳንዶቹ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በተለይ ምርጫን በተመለከተ በደንብና መመርያዎቻቸው ያካተቱትን አሠራርና ደንቡንም የሪፖርተር ዝግጅት ክፍል እንደተመለከተው ከሆነ፣ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ መምረጥም ሆነ መመረጥ እንደማይቻል ያሳያል፡፡

በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሆነው በዜግነት የሌላ አገር የሆኑ አንዳንድ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ በዚህ ጉዳይ የአገሪቱን ሕግ በመጥቀስ የሚከራከሩ አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 270/1994 የተደነገገው እንደሚከተለው ያስቀምጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዙ የውጭ ዜጎች መብቶችን በተመለከተ፣ በክፍል ሁለት አንቀጽ አምስት፣ ቁጥር ስድስት የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች በመጠቀም ረገድ በውጭ ዜጎች ላይ በሕግ በመመርያ ወይም በአሠራር ልምድ የተጣሉ ገደቦችና የሚደረጉ ልዩነቶች አይመለከትም፡፡

ገደቦች፣ በዚህ አዋጅ አንቀጽ አምስት የተደነገገው ቢኖርም፣ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዘ የውጭ ዜግነት ያለው ሰው፣ በተራ ቁጥር አንድ በማንኛውም በመንግሥት ደረጃ በሚካሄድ ምርጫ የመምረጥና የመመረጥ መብት አይኖረውም፡፡ በተራ ቁጥር ሁለት ደግሞ በማንኛውም የአገር መከላከያ የአገር ደኅንነት ወይም በውጭ ጉዳይና በመሰል የፖለቲካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በመደበኛነት ተቀጥሮ መሥራት እንደማይችል ይደነግጋል፡፡

ይህንኑ የሕግ ድንጋጌ አስመልክቶ በተለይም ‹‹ገደቦች›› ተብለው ከተቀመጡት የሕግ ድንጋጌዎች አንፃር ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያተኞች፣ የመንግሥት አስተዳደርና አሠራር ውስጥ የውጪ ዜጎችን ማሳተፍ በአዋጅም ሆነ በሌሎች የሕግ ማዕቀፎች ውስጥ የተከለከለ መሆኑን ያስቀምጣሉ፡፡

የቅርጫት ኳስ አመሠራረትና አሁን የሚገኝበት ደረጃ

ኢትዮጵያ በቅርጫት ኳስ ታሪክ ከግማሽ ክፍለ ዘመን የተሻገረ ቆይታ እንዳላት ይነገራል፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ታሪክ ከተካተቱት አምስት የኦሊምፒክ ስፖርቶች አንዱ ቅርጫት ኳስ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ምንም እንኳ በዚህ ደረጃ ሊጠቀስ የሚችል ተሳትፎ ባይታይበትም፣ ስፖርቱ ከትምህርት ቤቶች (እሱም በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች) ማለፍ ሳይችል ቆይቷል፡፡ የችግሩ ምንጭ ከሆኑት መካከል ደግሞ ለቅርጫት ኳስ የሚሰጠው ትኩረት እየቀነሰ መምጣት አንዱ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ፡፡ በታሪክ አጋጣሚ ስፖርቱን እንዲመሩ የሚሾሙ የፌዴሬሽን አመራሮችም በመስኩ ብቻ ሳይሆን በአቅምም ሆነ በችሎታ ይህ ነው ሊባል የሚችል ልምድና ተሞክሮ ሳይኖራቸው ቦታውን የሚቆናጠጡ ሆነው መገኘታቸው እንደ አንድ ምክንያት ተደርጎም ይጠቀሳል፡፡

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አባል ለመሆን ዕውቅና ካገኘችባቸው የስፖርት ዓይነቶች አንዱ ከመሆኑም በላይ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመርያ በሆኑት ትምህርት ቤቶች ማለትም ዳግማዊ ምኒልክ፣ ተፈሪ መኰንን፣ መድኃኔዓለምና ኮከበ ጽባሕ በመሳሰሉት ትምህርት ቤቶች ከውጭ መጥተው በመምህርነት ሲያገለግሉ በነበሩ አስተማሪዎች አማካይነት ቅርጫት ኳስ በስፋት ይዘወተር እንደነበር  አቶ ይመር ያወሳሉ፡፡

በቡድን ደረጃም የአራራት፣ የኦሊምፒያኮስና በሠራዊቱ በተቋቋሙ ቡድኖች አማካይነት ከፍተኛ ተወዳጅነት ነበረው፡፡ በደርግ ዘመን ስፖርቱ ከትምህርት ቤት ቡድኖች እስከ ክለብ ድረስ ጠንካራ የሕዝብ ተሳትፎ እንደነበረው የሚናገሩት አቶ ይመር፣ ስፖርቱ በምሥራቅ አፍሪካ ደረጃም ሊጠቀስ የሚችል ስምና ዝና አትርፎ የነበረበትን ወቅት ጭምር ያስታውሳሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት በወንዶች ዘጠኝ፣ በሴቶች አምስት ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ እንደሚወዳደሩ የሚናገሩት ኃላፊው፣ እነዚህ ሁሉ ውድድሮች የሚከናወኑት ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት በሚበጀትለት 300,000 ብር መሆኑ ሊዘነጋ እንደማይገባው ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ይህንን ስፖርት ወደ ቀድሞ ስምና ዝናው ለመመለስ በአቅምም ሆነ በችሎታ ጠንካራ የሆኑ አመራሮች ሊኖሩት የግድ የሚልበት ወቅት ላይ እንደሚገኝ ጭምር ያስረዳሉ፡፡

 

 

Standard (Image)

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለአራተኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ

$
0
0

የሪያል ማድሪድ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የዓመቱ ኮከብ ተጨዋችነትን ክብር ለአራተኛ ጊዜ አሸናፊ ሆኗል፡፡ የሌስተር ሲቲው አልጀሪያዊው ሪያድ ማሕሬዝ ደግሞ የቢቢሲ የአፍሪካ የዓመቱ ኮከብ ተጨዋችነትን ሽልማት አግኝቷል፡፡

ፊፋና የፈረንሣዩ ፉትቦል ሜጋዚን እ.ኤ.አ. ከ2010 ጀምሮ በጋራ ሲያዘጋጁት በቆዩት የዓመቱ የዓለም ኮክብ ተጨዋች ምርጫ የዘንድሮው አሸናፊ ፖርቱጋላዊ ክርስቲያኖ ሮናልዶና አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ማንንም ጣልቃ ሳያስገቡ ክብሩን በማግኘትና ተጠቃሽ በመሆን ለዘጠኝ ተከታታይ ዓመታት ዘልቀዋል፡፡ የባሎንዶር መሥራቹ ፍራንስ ፉትቦል ሜጋዚን የዘንድሮውን ሽልማት ያዘጋጀው ቀደም ሲል በነበረበት አግባብ ከፊፋ ጋር ያለውን ግንኙነት አቋርጦ ሲሆን፣ ይኽም ሮናልዶን የመጀመሪያ ያደርገዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ለዘንድሮ የባሎንዶር ዕጩ በመሆን ከቀረቡት 20 ተጨዋቾች መካከል ክብሩን ለአራተኛ ጊዜ ያሸነፈው ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ አምስት ጊዜ ያሸነፈው ሊዮኔል ሜሲና የአትሌቲኮ ማድሪዱ አንቶኒ ግሬዝማን ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እ.ኤ.አ. በ2008 የመጀመርያውን የኮከብነት ክብር ሲቀዳጅ፣ አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ደግሞ ከ2009 ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ዓመት አግኝቷል፡፡ ሮናልዶ እንደገና በ2013 እና በ2014 የክብሩ ባለቤት በመሆን ሲያሸንፍ፣ አርጀንቲናዊው የባርሴሎና ኮከብ ደግሞ ሁለት ተከታታይ ዓመታትን አሸንፎ በአጠቃላይ አምስት ጊዜ የክብሩ ባለቤት በመሆን ክርስቲያኖን በመምራት ላይ ይገኛል፡፡ ለስድስተኛ ጊዜ የዘንድሮውን ክብር ማግኘት የነበረበት ራሱ ሜሲ ሊሆን እንደሚገባ የሚከራከሩ በርካቶች መሆናቸው በምርጫው ዙሪያ የቀረቡ ዘገባዎች ያስረዳሉ፡፡

በውድድር ዓመቱ የሁለቱ ተጨዋቾች የስኬት መጠን በመከራከሪያነት በማቅረብ በምርጫው ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሸናፊ መሆን ይገባዋል የሚሉት፣ ክርስቲያኖ ከሪያል ማድሪድ ጋር ያሳካው የአውሮፓ ክለቦች ዋንጫና በአውሮፓ ዋንጫ አገሩ ፖርቱጋልን ሻምፒዮን ማድረግ መቻሉ ለክብሩ ተጠቃሾች ሆነዋል፡፡ ሁለቱ ተጨዋቾች በውድድር ዓመቱ በክለብም ሆነ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ያስቆጠሯቸው ጎሎችና ለቡድን ተጨዋቾቻቸው ያቀበሏቸው ኳሶች በዝርዝር ቀርበው ድምፅ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ክርስቲያኖ ክብሩን ካገኘ በኋላ፣ ‹‹አሸንፋለሁ ብዬ አልጠበቅኩም፡፡ ለዚህ ክብር የፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድንና ለሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች የላቀውን ድርሻ ተወጥተዋል፤›› በማለት ለቡድን አጋሮቹ ያለውን ክብር ገልጿል፡፡

ለዘንድሮው ባሎንዶር ክብር ዕጩ ሆነው ከተመረጡት 20 ተጨዋቾች መካከል በተራ ቁጥር ሰባት የተቀመጠው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያለፈው ዓመት ሻምፒዮን የሌስተር ሲቲው አልጄሪያዊ ሪያድ ማሕሬዝ የቢቢሲ የአፍሪካ የዓመቱ ኮከብ በመሆን አሸናፊ ሆኗል፡፡

ለአፍሪካ የዓመቱ ኮከብ ተጨዋችነት ክብር ለመብቃት ለመጨረሻው ምርጫ ከቀረቡት ጋቦናዊ የዶርትሞንዱ ኤሜሪክ አቦሚያንግ፣ የዌስትሐም ዩናይትዱ ጋናዊው አንድሬ አዩው፣ የሊቨርፑሉ ሰይዶ ማኔና የማንችስተር ሲቲው ያያ ቱሬ ናቸው፡፡ አሸናፊው ሪያድ ማሕሬዝ ክብሩን አስመልክቶ፣ ታላቅ ኩራት እንደተሰማው ገልጾ፣ ‹‹የአፍሪካ የዓመቱ ኮከብ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው፤›› ብሏል፡፡

Standard (Image)

የኮካ ኮላ ካምፓኒና የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን የግማሽ ሚሊዮን ብር የስፖንሰርሽፕ ስምምነት አደረጉ

$
0
0

ብስክሌትን ጨምሮ በአገሪቱ የተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው የመንግሥት እጅ ከመጠበቅ ያለፈ ሚና ሳይኖራቸው ቆይተዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ማክሰኞ ታኅሣሥ 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በኮካ ኮላ ካምፓኒና በአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን የተደረሰው የግማሽ ሚሊዮን ብር የስፖንሰር ሽፕ ስምምነት ይበል የሚያሰኝ ሆኗል፡፡

በአዲስ አበባ ጦር ኃይሎች አካባቢ የሚገኘው የካምፓኒው ፋብሪካ ቅጥር ግቢ የተደረሰው ስምምነት፣ ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ መሆኑ የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን የቦርድ አባል አቶ ነብዩ ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡ በኮካ ኮላ ካምፓኒ የምሥራቅ አፍሪካ ማናጀር ሚስተር ዣቪየር ሴልጋን በበኩላቸው በብስክሌት አቅሙና ክህሎቱ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች እነዚህን በመሰሉ ስምምነቶች ማገዝ ለስፖርቱ ብቻ ሳይሆን ለኩባንያው ጭምር ትልቅ ስኬት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ብስክሌት በአገሪቱ መስፋፋት ይችል ዘንድ መንቀሳቀስ ከጀመረ በርካታ ዓመታትን ቢያስቆጥርም፣ በፋይናንስ አቅምና መሰል ችግሮች ስፖርቱ የምሥረታውን ያህል ማደግ ሳይችል መቆየቱ የዘርፉ ሙያተኞች ይናገራሉ፡፡ ስፖርቱን በበላይ ጠባቂነት ከዘጠኝ ዓመት በላይ እንዳገለገሉ የሚነገርላቸው አቶ ነብዩ ሳሙኤል እዳወሱት የፋይናንስ ችግር ለዕድገቱ ማነቆ ሆኖ መቆየቱን ገልጸው፣ ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ የግድ እንደነዚህ ዓይነት ስምምነቶች ያስፈልጋሉ፡፡

ስፖርት በመንግሥት ድጎማ ብቻ ከሚንቀሳቀስባቸው አገሮች ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ከሆኑ ተርታ እንደምትጠቀስና የዓለምን ተጨባጭ ሁኔታ በማጣቀስ በአገሪቱ ያለውን አሠራር የሚተቹ አሉ፡፡ በኮካ ኮላ ካምፓኒ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ስምምነቱ ሲፈጸም በቦታው የነበሩ የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ተወዳዳሪዎችም ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ተወካይ አቶ በኃይሉ በቀለ በሥነ ሥርዓቱ ከተገኙት ይጠቀሳሉ፡፡ እንደ ተወካዩ ብስክሌትን ጨምሮ በአገሪቱ ለሁሉም ስፖርቶች ዕድገት መቀጨጭ በመንግሥት ድጎማ ብቻ የሚኬድበት አግባብ በመንስዔነት እንደሚጠቀስ ገልጸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በኮካ ኮላ ካምፓኒና በአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሽን መካከል የተደረሰው ስምምነት የሚደግፈው መሆኑ እንደተጠበቀ፣ ሌሎችም እንደ ውኃ ዋናና ጠረጴዛ ቴኒስ የመሳሰሉ በአርአያነት ሊጠቀሙበትና ሊከተሉት እንደሚገባ ጭምር ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ከፊታችን እሑድ ታኅሣሥ 9 ቀን ጀምሮ ለ17 ቀናት የሚቆይ የኮካ ኮላ ሻምፒዮንና ውድድር እንደሚያከናውንም አቶ ነብዩ በዕለቱ ገልጸዋል፡፡

የኮካ ኮላ ካምፓኒ ከብስክሌት ፌዴሬሽን በተጨማሪ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ባደረገው የስፖንሰርሽፕ ስምምነት ዕድሜያቸው ከ15 እና ከ17 ዓመት በታች አገር አቀፍ ዓመታዊ የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ውድድሮችን በማከናወን ላይ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንደ ሚስተር ዣቪየር ሴልጋን ገለጻ ከሆነ፣ ካምፓኒያቸው እንደ አስፈላጊነቱ በሌሎች ስፖርቶችም ተመሳሳይ ስምምነቶች በማድረግ አጋርነቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

Standard (Image)

‹‹በስፖርቱ ከነበር ታሪክ ወጥተን ትውልዱን ጠቅመን ልንጠቀምበት ይገባል››

$
0
0

አቶ ነብዩ ሳሙኤል፣ የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን የበላይ ጠባቂ

በአገሪቱ የተለያዩ ስፖርቶች ቢኖሩም ሁሉም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው የሚወሰነው ከመንግሥት ቋት በሚበጀትላቸው ፋይናንስ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይኼ ስፖርቱ በተለይም በአሁኑ ወቅት ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ አኳያ ትክክለኛ አካሄድ እንዳልሆነ የሚናገሩ አሉ፡፡ ከ1990ዎቹ ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ ዕውን የሆነው የስፖርት ፖሊሲ ስፖርቱ በጊዜ ሒደት ከመንግሥት ተደጓሚነት ወጥቶ፣ ሕዝባዊ አደረጃጀት ኖሮት ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት ሁኔታ መኖሩን ያመለክታል፡፡ እስካሁን በጣት የሚቆጠሩ የእግር ኳስ ክለቦች ካልሆነ አብዛኛው የአገሪቱ ስፖርቶች ከመንግሥት ድጎማ መውጣት አልቻሉም፡፡ ከሦስት አሠርታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ የሚናገሩት አቶ ነብዩ ሳሙኤል፣ የአገሪቱ ስፖርት ራሱን ሸጦ አቅሙን ማጠናከር በማስቻል ረገድ በጣም ኋላ ቀር መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በአገሪቱ በርካታ ካምፓኒዎችና ድርጅቶች እንደመኖራቸው ስፖርቱን ተጠቅመው አገልግሎታቸውን የሚሸጡበት ዕድል የለም፡፡ ቢኖርም እጅግ በጣም ጥቂት ነው ይላሉ፡፡ በማስታወቂያ ረገድ ያለው ግንዛቤ ገና ብዙ የሚቀረው ስለመሆኑም ያምናሉ፡፡ አቶ ነብዩ ከግል ሥራቸው በተጨማሪ የኢትዮጵያ ጎልፍ አሶሴሽን ፕሬዚዳንትና የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን የበላይ ጠባቂ ናቸው፡፡ የስፖርት ተቋማትን የሚያስተዳድሩ አካላት ዘርፉ ከመንግሥት ድጎማ ተላቆ ጠንካራ የፋይናንስ አቅም መፍጠር የሚያስችሉ ግንዛቤዎች ላይ ምንም እየሠሩ እንዳልሆነና በካምፓኒዎችና በስፖርት ተቋማት መካከል ከፍተኛ የግንኙነት ክፍተት እንዳለ ያስረዳሉ፡፡ በእነዚህና በሌሎችም መሰል የስፖርት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ አቶ ነብዩ ሳሙኤልን ደረጀ ጠገናውአነጋግሯቸዋል፡፡  

ሪፖርተር፡- የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን በአገሪቱ ቀደምት ከሚባሉ ፌዴሬሽኖች ተጠቃሽ ነው፡፡ ውጤቱ ደግሞ ቀደም ሲል የነበረውን እንኳ ማስቀጠል እየቻለ አይደለም፡፡ የስፖርቱ የበላይ ጠባቂ እንደመሆንዎ ምክንያት የሚሉት ምንድነው?

አቶ ነብዩ፡- ለዚህ ጥሩ ማሳያና መልስ ሊሆን የሚችለው ዓለም ላይ ያለውን ተሞክሮ መመልከት ነው፡፡ እንኳን በአሁኑ ወቅት ቀደም ሲል ጀምሮ ስፖርት ቀርቶ ማናቸውም የቢዝነስ ተቋማት በራሱ የሚንቀሳቀስ የለም፡፡ በአገራችን ያለው ተሞክሮ ግን አሁን አሁን ካልሆነ አገልግሎት የመሸጥ ግንዛቤ ገና ነው፡፡ ለአገሪቱ ሁሉም ስፖርቶች ለዕድገታቸው ማሽቆልቆል ትልቁ ችግር የፋይናንስ አቅም ነው፡፡ ስፖርቱ በዚህ ረገድ የመንግሥት ቋት ጠብቆ ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ ብስክሌቱም የዚሁ አካል ነው፡፡ የፋይናንስ አቅም ስለሌለው ቀጣይነት ያለው ውጤት ማስመዝገብ አልቻለም፡፡ እንዲያውም ከነበረው ወርዷል ማለት ይቻላል፡፡ በኃላፊነት በነበርኩባቸው ዓመታት እንኳ ስፖርቱን ወደ ኅብረተሰቡ በማስረጽ ጠንካራ የሚሆንበት አማራጭ ለመፍጠር የተለያዩ ስያሜዎችን በመስጠት የክልል ቡድኖች በማካተት ጭምር ውድድሮችን አከናውነናል፡፡ ከተደረጉት ውድድሮች ‹‹ጉዞ ወደ ባህር ዳር›› በሚል ሰባት ቀን የፈጀ የብስክሌት ውድድር ይጠቀሳል፡፡ በወቅቱ ለአንድ ሳምንት ያህል ሞቅ አለና እንደገና ቀዘቀዘ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቀደም ሲል ለመግለጽ እንደሞከርኩት ማስቀጠል የሚችል የፋይናንስ አቅም መጥፋት ነው፡፡ ይኼ የብስክሌቱ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ስፖርቶች ችግር ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የስፖርቱ ውጤቱ ብስክሌቱን ጨምሮ ለአገልግሎት መቅረብ የሚችልበት ደረጃ ላይ አልደረሰም፡፡ ለዚህ የሚሉት ይኖርዎታል?

አቶ ነብዩ፡- ብስክሌትና ሌሎች ጥቂት ስፖርቶች ውጤት የላቸውም በሚለው ልንስማማ እንችላለን፡፡ አትሌቲክሳችን እኮ ዓለም ላይ ትልቅ ዕውቅና ካላቸው አንዱ ነው፡፡ በአትሌቲክሱ እንደነ ኬንያውያን፣ ጃማይካውያንና አሜሪካውያንን ያህል እየተጠቀምንበት አይደለም፡፡ ስለዚህ ችግሩ ውጤቱ ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ አገልግሎትን በመሸጥና በመጠቀም ረገድ ግንዛቤያችን ገና ነው፡፡ እርግጥ ነው አሁን አሁን ጅምሮች አሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ባለፈው ሳምንት የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሸን የኮካ ኮላ ካምፓኒ ከሆነው ከኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ጋር ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የስፖንሰርሽፕ ስምምነትን አድርጓል፡፡ ሒደቱ እንዴት ነበር?

አቶ ነብዩ፡- ሒደቱ ያን ያህል አስቸጋሪ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ይዘን የቀረብነው ፕሮፖዛል አሳማኝ ነበር፡፡ ለዚያም ነው ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የግማሽ ሚሊዮን ብር ስምምነት ላይ የደረስነው፡፡ ይኼ ለሌሎችም ስፖርቶች ጥሩ ተሞክሮ ይሆናቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ምክንያቱም አገልግሎትን መሸጥና መጠቀም ልመና ወይም ድጎማ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡ ጥቅሙ የጋራ ነው፡፡ የጋራ ለሆነ ነገር ደግሞ በጋራ መሥራትና ማደግ ዓለም ላይ የሚሠራበት እውነታ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ለብስክሌት የያዛቸው በአብዛኛው ታዳጊ ወጣቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ወጣቶች በውድድር መድረክ ጎልተው መውጣት የሚችሉት ከወዲሁ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል ሲደረግላቸው ብቻ ነው፡፡ በአቅም እጥረት ትልቅ ህልም የሰነቁ ታዳጊ ወጣቶች ሕይወታቸውን በአልባሌ ነገር እንዲያሳልፉ የሚገደዱ የምናውቃቸው በርካታ ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ ማንኛውም በአገሪቱ የሚገኝ ካምፓኒ ይሁን ድርጅት ማኅበረሰብን የማገልገል ኃላፊነት እንዳለበት ሊታወቅ ይገባል፡፡   

ሪፖርተር፡- እንዲያ ከሆነ ታዲያ መሠረታዊ ችግር የሚሉዋቸው ምንድናቸው?

አቶ ነብዩ፡- በዋናነት የግንዛቤና የግንኙነት ክፍተት ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ኮካ ኮካ ብስክሌቱን ስፖንሰር እንዲያደርግ ቀርበን ስንጠይቀው ፈቃደኝነቱን የገለጸልን ምንም ሳያቅማማ ነው፡፡ ለምን ካምፓኒው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደመኖሩ ከሚያገኘው ትርፍ ላይ የአገሪቱን ወጣቶች በስፖርት ተሳትፎው ተጠቃሚ እንዲሆኑ አንዱ የኃላፊነት ድርሻው እንደሆነ ያውቃልና ነው፡፡ ነገር ግን ካምፓኒው ስፖንሰር ከማድረጉ በፊት በአቀራረቡ በኩል ያለው ሁኔታ ይወስነዋል፡፡ ምክንያቱም ካምፓኒው ከብስክሌቱ ጋር አብሬ ብሠራ የማገኘው ጥቅም ምንድነው? የሚለውን መጠየቁ ስለማይቀር ያንን በአጥጋቢ ሁኔታ የማሳመን ሥራ መሥራት የግድ ነው፡፡ ስፖንሰሮች ከስፖርቱ ጋር አብረው በመሥራታቸው የሚያገኙት ጥቅም የግድ የገንዘብ ብቻ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም፡፡ የሞራልና አገርን የመጥቀም ጉዳይም ነው፡፡ የስፖርት ተቋማት ደግሞ እነዚህን ነገሮች በዝርዝር ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህ በኩል ቀደም ሲልም ለመግለጽ እንደሞከርኩት የግንዛቤ ክፍተት አለ፡፡ ቀጣይ ግን የአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገትም ስለሚያስገድደን አጠናክረን እንደምንገባበት እምነቱ አለኝ፡፡ ጀምረነዋልም፡፡ ለጊዜው ያለው ችግር ግን ስፖንሰር የማድረግ አቅም ያላቸው ካምፓኒዎችና ድርጅቶችን በማሳመኑ ረገድ ክፍተት ስላለብን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የስፖርቱ አመራሮች እንደ ቴክኒክና ታክቲክ ለዚህም ዕውቀቱና ግንዛቤ ያላቸው ሙያተኞች እጥረት መሆኑን መውሰድ እንችላለን ማለት ነው?

አቶ ነብዩ፡- የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ በግልጽ የሚታይ የግንዛቤ ክፍተት አለብን፡፡

ሪፖርተር፡- አዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን አሁን እርስዎ ከሚሉት አኳያ ምን እያደረገ ነው?

አቶ ነብዩ፡- ችግሩ አገር አቀፍ ነው፡፡ ነገር ግን ከኮካ ኮላ ጋር ለተደረገው ስምምነት ፌዴሬሽኑ መሥራት ያለበትን ሠርቶ ነው ጥያቄውን ያቀረበው፡፡ ምክንያቱም ስምምነቱ በተከናወነበት ዕለት ታዳጊ ወጣት ብስክሌተኞች ከነሙሉ ትጥቃቸው እንዲገኙ ነው ያደረግነው፡፡ የካምፓኒው ኃላፊዎች በሁኔታው በጣም ነበር የተደነቁት፡፡ ሌላው ለስፖርቱ ዕድገት እንደ ስፖንሰሮቹ ሁሉ ሚዲያውም ትልቅ ድርሻ አለው፡፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዓለም ላይ አሁን ያለውን ቅርፅ እንዲይዝ የሚዲያው ሚና ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡ እርግጥ ነው በተደራሽነት ረገድ የአቅም ልዩነት እንዳለ ይገባኛል፡፡ ግን ለራስ ቅድሚያውን መስጠት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ ቀደምቱ ብስክሌተኛ አቶ ገረመው ደምቦባ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስለብስክሌት ሳይናገሩ ያለፉበት ጊዜ የለም፡፡ ያንን ሚዲያው ተገቢን ትኩረት ሰጥቶ ለኅብረተሰቡ እንዲደርስ በማድረጉ ግን በጣም አናሳ በመሆኑ ጩኸታቸው ፍሬ ማፍራት አልቻለም፡፡

ሪፖርተር፡- ሚዲያው መረጃውን ማግኘት የሚችልበት የተመቻቸ ነገር አለ ብለው ያምናሉ?

አቶ ነብዩ፡- ችግሮች እንዳሉ ይገባኛል፡፡ መገናኛ ብዙኃን ለአውሮፓ እግር ኳስ ቅድሚያ እንዲሰጡ የሆነው አንዱ ምክንያትም የአገር ውስጥ መረጃ የሚገኝበት ዕድል ጠባብ መሆኑ ነው፡፡ እኔ ከአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን በተጨማሪ የኢትዮጵያ ጎልፍ አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ነኝ፡፡ ኢትዮጵያ በቅርቡ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጎልፍ ኮርስ (ማዘውተሪያ) ባለ 18 ጉድጓድ ባለቤት ሆናለች፡፡ ብዙ ጊዜ የጎልፍ ሻምፒዮናዎችን ስናዘጋጅ መገናኛ ብዙኃን እንጠራለን፡፡ በተለይ በኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙኃን የምናገኘው ሽፋን ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጋር ሲነፃፀር የሰማይና የምድር ያህል ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ጨርሶ የማይቀርብበት ጊዜም አለ፡፡ የስፖርቱን ውድቀት የምናፋጥነው ራሳችን ነን፡፡ በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ጎልፍ አሶሴሽን ገንዘብ እየከፈለ ልክ እንደማስታወቂያ ሽፋን እንዲያገኝ ለማድረግ ዕቅድ አለው፡፡ ምክንያቱም ከበቂ በላይ የጎልፍ ስፖንሰሮች አሉን፡፡ ስፖርቱ በቂ ሽፋን እንዲያገኝም ይፈልጋሉ፡፡ ኅብረተሰቡ ስለአገሩ ስፖርት እንዲያውቅ ትልቁ የፕሮፓጋንዳ ማሽን ተብሎ የሚታሰበው ሚዲያው ነው፡፡ በአገሪቱ አቅሙም ክህሎቱም ያለው በየስፖርቱ አለ፡፡ ተገቢው እገዛና የሞራል ድጋፍ ግን እየተደረገለት አይመስለኝም፡፡

ሪፖርተር፡- የአገር ውስጥ ባለሀብቶች እርስዎ በሚሉት ደረጃ በስፖርቱ ለመጠቀም ፍላጎቱ አላቸው ብለው ያምናሉ?

አቶ ነብዩ፡- የግንኙነትና የመረጃ ክፍተት ካልሆነ በቀር አሉ በሚለው ነው የምስማማው፡፡ ግን ደግሞ በሚከፍሉት ልክ ተመጣጣኝ ሽፋን ይጠብቃሉ፡፡ በአሜሪካ ‹‹ሱፐር ቦል›› በመባል የሚታወቀው የኮካ ኮላ ምርት ለ30 ሰከንድ ማስታወቂያ የሚከፍለው ሦስት ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ ይህ ማለት የኮካ ኮካ ካምፓኒን ብቻ ስንመለከት ማለት ነው፡፡ ሌሎች ካምፓኒዎችም ተመሳሳይ ነው፡፡ አሁንም ተስፋ አደርጋለሁ፣ ግንዛቤው እየመጣ ስለሆነ የስፖርቶቻችን ትንሣኤ ሩቅ እንደማይሆን እጠብቃለሁ፡፡ በነገራችን ላይ ብስክሌቱን እንዳግዝ የገፋፋኝ የኢቢሲው ጋዜጠኛ ሰለሞን ገብረእግዚአብሔር ነው፡፡ ከብስክሌትና ጎልፍ በተጨማሪ ይህ ካምፓኒ የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን ማገዝ የሚችልበትን እያመቻችሁ ነው፡፡ ስለጉዳዩ ከካምፓኒው ማናጀር ጋር ተነጋግረን እሱ ራሱ በጠረጴዛ ቴኒስ በፕሮፌሽናል ደረጃ ተወዳዳሪ እንደነበር ገልጸልኝ ነው ይሁንታውን የሰጠኝ፡፡ ፕሮፖዛሉ እየተዘጋጀ ስለሆነ መጠኑን ለመግለጽ እቸገራለሁ፡፡ በሁሉም መስክ አቅሙ አለ፤ ግን እየተጠቀምንበት አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ በቅርቡ ዕውን የሚሆነው ባለ 18 ጉድጓድ የጎልፍ ኮርስ (ማዘውተሪያ) ‹‹ኦፕን ኢትዮጵያ›› በሚል ስያሜ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ እናዘጋጃለን፡፡ ለሻምፒዮናው አሥር ሚሊዮን ብር ለማግኘት ዕቅድ አለን፡፡ በእርግጠኝነት እናሳካዋለን፡፡ በሻምፒዮናው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ፕሮፌሽናሎች ይሳተፋሉ፡፡ ለአሸናፊው በኢትዮጵያ እስከ 300,000 ብር ሽልማት እንሰጣለን፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ የበርካታ ታላላቅ አገሮች አየር መንገዶች ከወዲሁ ቃል መግባት ጀምረዋል፡፡ ስለሆነም የአገራችን ስፖርት አንድ ዕርምጃ ወደፊት እንዲራመድ ፍላጎቱ ያለን የስፖርት አመራሮች ከልብ መንቀሳቀስ ከቻልን በአገሪቱ የአቅም ችግር የለም፡፡ የኢትዮጵያ ብስክሌት እንደነገረመው፣ ሙሴ ዮሐንስና ሌሎችም በርካታ ስመ ጥር ተወዳዳሪዎች የነበሩበት ነው፡፡ አሁን ለምን ጠፋ ብለን ልንቆጭና ልንቆረቆር ይገባል፡፡ ከ‹‹ነበር›› ታሪክ ወጥተን ትውልዱን ጠቅመን ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ በአሜሪካ ማንኛውም ቢዝነስ 25 በመቶው በጀቱ ከማስታወቂያ ነው፡፡ ወደ ስፖርተኛው ስንመጣ ደግሞ ለምልመላ መጀመሪያ መመልከት የሚኖርብን ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች ላይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ አሁን ባለው ሁኔታ ውጤት ጠፋ ካልሆነ ለውጤት የሚያበቁን ታዳጊ ወጣቶች ላይ የምንሠራው ሥራ የለም፡፡ እንዴት ነው ታዲያ ነገ በዓለም አቀፍ መድረክ ውጤት የምንጠብቀው? ስለዚህ መለስ ብለን ታዳጊ ወጣቶቻችንን የምንመርጥበትን ሥርዓት መመልከት ይኖርብናል፡፡ የሌሎች አገሮችን ተሞክሮ በመመልከት ወደ እዚያ ሥርዓት መግባት ያስፈልጋል፡፡ አሠልጣኞቻችን ስለአሠለጠኑ ብቻ በቂ ዕውቀት አላቸው? እነዚህንና መሰል ክፍተቶቻችን በደንብ መመልከት ካልቻለን ከዓለም ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ተፎካካሪ መሆን ይከብደናል፡፡ በማስታወቂያ ደረጃም ያለን ግንዛቤ እንደዚሁ ሊታይ ይገባዋል፡፡ በዚህ ደረጃ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነኝ፣ ጎልፍ ላይ የምንሠራው ሥራ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በፊት የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ የጎልፍ ሻምፒዮና አዘጋጅታ ነበር፡፡ ለዚያ ሻምፒዮና የዓለም አቀፉን የጎልፍ እንቅስቀሴ በበላይነት የሚመራው ‹‹አርኤንድኤ›› እገዛ እንዲያደርግልን ጠይቀነው 10,000 ዶላር ነው የፈቀደልን፡፡ ከዚያ በፊት ለስፖርቱ የሚውል ቁሳቁስ ቢልክልንም በራሳችን ድክመት እስካሁን በእጃችን አልገባም፡፡ ብስክሌቱም ዓለም አቀፉ ማኅበር ስላለው ሥርዓቱን ተከትለው መጠየቅ ይኖርብናል፡፡

ሪፖርተር፡- ገንዘቡ ከተገኘ በኋላ ለምሳሌ ኮካ ኮካ ካምፓኒ ለብስክሌት ፌዴሬሽን ግማሽ ሚሊዮን ብር ሰጥቷል፡፡ ይህ ገንዘብ በትክክል ለታሰበለት ዓላማ መዋል አለመዋሉን የምትቆጣጠሩበት አሠራርስ እንዴት ነው፡፡ ተጠያቂነቱና ግልጽነቱ በምን ይገለጻል?

አቶ ነብዩ፡- እውነቱን ለመናገር እስካሁን ባለው ገንዘቡን ከማምጣት ባለፈ አጠቃቀሙ እንዴትና በምን አግባብ ነው ስለሚባለው ምንም ግንዛቤ የለኝም፡፡ ጠይቄም አላውቅም፡፡ ጥሩ ጥቆማ ነው፡፡ እንደተባለው ገንዘቡ ምን ላይ ዋለ? የሚለውን መመልከት ተገቢ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡

 

Standard (Image)

እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፓርላማ ማብራሪያ እንዲሰጥ ታዘዘ

$
0
0

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እግር ኳሱን ለመምራትና ለማስፋፋት እያከናወነ ያለውን የአሠራር ሥርዓት በተመለከተ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ባቀረበው የክዋኔ ሪፖርት ላይ በፓርላማ ለመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ማብራሪያ እንዲሰጥ ታዘዘ፡፡

በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች የእግር ኳሱ መታወቅና የክለቦች መቋቋምን ተከትሎ ስፖርቱን በበላይነት የሚመራ አካል የስፖርት ጽሕፈት ቤት በሚል ስያሜ በ1936 ዓ.ም. በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሥራ መቋቋሙ መዛግብቶች ያስረዳሉ፡፡ በወቅቱ የነበረው ጽሕፈት ቤት በአደረጃጀት፣ በሰው ኃይልና በፋይናንስ የተጠናከረ ባለመሆኑ ምክንያት ጽሕፈት ቤቱ በፌዴሬሽን ደረጃ እንዲቋም በተደረሰው ስምምነት መሠረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ1941 ዓ.ም. ሊመሠረት መቻሉ ጭምር ይነገራል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ከተመሠረተ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ እንዳስቆጠረ የሚነገርለትን ብሔራዊ ፌዴሬሽን፣ በ2008 የውድድር ዓመት ያከናወነውን የዕቅድ ክዋኔ ኦዲት አድርጎ ለፓርላማው የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለቀረበው ክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ማብራሪያ እንዲሰጥ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ዓርብ ታኅሣሥ 14 ቀን 2009 ዓ.ም. ጥሪ ተደርጎለታል፡፡ ይህንኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡  

የኦዲት ሪፖርቱ በክፍተትነት ከተመለከታቸው አሠራሮች መካከል፣ ፌዴሬሽኑ በወቅቱ ለነበረው ስፖርት ኮሚሽን ዓመታዊ ዕቅድና ክንውን ሪፖርት መላኩን በተመለከተ ስለሁኔታው የተቋሙ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ፣ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለኮሚሽኑ ለመላክ አደረጃጀቱ የማይፈቀድለት እንደሆነ በመግለጽ፣ መላክ እንደሌለበት በሰጠው አስተያየት የገለጸ ቢሆንም፣ ማስረጃው እንዳልቀረበለት ነው ያስረዳው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለፌዴሬሽኑ በተላከለት ረቂቅ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ በጽሑፍ በሰጠው ምላሽ ደግሞ በአዲሱ የፌዴሬሽኑ አደረጃጀት የክለሳ ጥናት፣ ተፈላጊ የሥራ መደቦችን ከኦዲት ጋር በማከል ተዘጋጅቶ የመጨረሻው የአፈጻጸም ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ አስተዳደራዊ መዋቅሩንና የሥራ መደቦችን ማሻሻያ ዝርዝር ሰነድ አያይዞ አቅርቧል፡፡ ሆኖም ዝርዝር ሁኔታው ለሚመለከተው አካል ቀርቦ ስለመጽደቁ መረጃው ባለመቅረቡና የተከለከለ መዋቅር ስለመሆኑ መቀበል እንደሚያዳግት የኦዲት ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ የተቀመጡ ግዴታዎችና ደንቦች በራሱ በፌዴሬሽኑ መተግበር አለመተግበራቸውን በተመለከተ፣ ረቂቅ ሪፖርቱ በጽሑፍ ከሰጠው ምላሽ ጋር ጥናት ተጠንቷል በማለት አያይዞ ያቀረበው ሰነድ እንደሚያሳየው ከሆነ፣ ለ2008 ዓ.ም. የቡድኖች አደረጃጀት መነሻ የቀረበ ሐሳብ እንጂ የተጠና ጥናት ባለመሆኑ ፌዴሬሽኑ የሰጠውን መልስ ለመቀበል እንደማይችልም ኦዲት ሪፖርቱ ያትታል፡፡

የፌዴሬሽኑን የገቢ አሰባሰብ ሥልቶችን በተመለከተ ስለሁኔታው አሁን ያለው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በነባራዊ ሁኔታ መግለጫው ላይ በሰጠው ምላሽ፣ ይህ ጉዳይ ቀድሞ በነበሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተፈጸመ በመሆኑ በዚሁ ዙሪያ በቂ መረጃ እንደሌለው መግለጹን ያስረዳል፡፡ ሆኖም በኦዲት ክዋኔ ሪፖርቱ ኃላፊዎቹ ይህን ይበሉ እንጂ፣ የተጠየቀው የተቋሙን አሠራር እንጂ የግለሰቦች ባለመሆኑ የተወሰኑ መረጃዎች በፌዴሬሽኑ ይኖራሉ ተብሎ ስለሚያምን የተሰጠው መልስ ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም ያሳያል፡፡

በፌዴሬሽኑ የሚሰጡ ሥልጠናዎች የክልሎችን የሥልጠና ፍላጎት ያገናዘበ መሆን አለመሆኑን በተመለከተ፣ የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተጠይቆ፣ ክልሎች ራሳቸውን የሚያስተዳድሩ በመሆኑ የሥልጠና ፍላጎታቸውን የመጠየቅ ግዴታ እንደሌለባቸው በተላከላቸው ነባራዊ ሁኔታ መግለጫ ላይ በሰጠው አስተያየት ገልጿል፡፡ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ይህን ይበል እንጂ ከፌዴሬሽኑ ሥልጣንና ተግባር መካከል አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር በክልልም ሆነ በፌዴራል ስፖርቱ እንዲስፋፋና እንዲያድግ ድጋፍ ማድረግ በመሆኑ የተሰጠው መልስ ተቀባይነት እንደሌለው ነው ያመለከተው፡፡

ለአሠልጣኞችና ለዳኞች መሥፈርት ተዘጋጅቶ ደረጃ መስጠትን በተመለከተ፣ ስለጉዳዩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በነባራዊ ሁኔታ መግለጫ ላይ በሰጠው ምላሽ በአገር አቀፍ ደረጃ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ አሠልጣኝነት ሥልጠና ምዘና በማከናወን ሰርተፊኬት በመስጠት ማረረጋገጫ እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጿዋል፡፡ ለረቂቅ ሪፖርቱ በጽሑፍ በተሰጠ ምላሽ ደግሞ፣ የአሠልጣኞች ደረጃ የተለያዩ አምስት መሆናቸው የተገለጸና ማስረጃም የተያያዘ ነው፡፡ የሚሰጠው ደረጃ ግን ከዓለም አቀፉ የደረጃ አሰጣጥ ጋር ለምን እንዳልተጣጣመ ምላሽና ማብራሪያ እንዳልተሰጠም ያሳያል፡፡

የብሔራዊ አሠልጣኞች መመልመያ መሥፈርትን በተመለከተ ፌዴሬሽኑ ለሪፖርቱ በጽሑፍ በሰጠው ምላሽ የፌዴሬሽኑ የአሠልጣኞች የመመልመያ መስፈርት ተዘጋጅቷል በማለት አያይዞ በቀረበው ማስረጃ ይገልጻል፡፡ ሆኖም በወቅቱ በነበረው ስፖርት ኮሚሽን ለሁሉም ፌዴሬሽኖች በ2006 ዓ.ም. የተዘጋጀ ረቂቅ ሰነድ እንጂ በየደረጃው ለሚገኙ ለሁለቱም ጾታዎች የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድኖች የሚቀጠሩ አሠልጣኞች መምረጫ መሥፈርት ተለይቶ አልቀረበም፡፡ በመሆኑም የብሔራዊ ቡድኖች አሠልጣኝ የመምረጫ መሥፈርት እንደየደረጃቸው አለመዘጋጀቱና በየጊዜው በቴክኒክ ኮሚቴው መመረጡ ፌዴሬሽኑ የሚያከናውነው ምርጫ ሁሉም በግልጽ ሊረዳው በሚችል መልኩ አለመሆኑ ምርጫውም አድሎአዊ ለሆኑ አሠራሮች የተጋለጠ ነው፡፡

ፌዴሬሽኑ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ከዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ደረጃ ጋር መጣጣም አለመጣጣማቸውን በተመለከተ፣ ፌዴሬሽኑ ለረቂቅ ሪፖርቱ በጽሑፍ ከሰጠው ምላሽ ጋር የውድድር ፕሮግራሞችን አያይዞ ያቀረበ ቢሆንም፣ በኦዲት ወቅት በናሙና ጥያቄ ያቀረበላቸው ክለቦች፣ አሠልጣኞችና ተጨዋቾች በሰሌዳው መሠረት እንደማይካሄድ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በወጣው ፕሮግራም መሠረት ውድድር ውድድሮቹ ተከናውነዋል በተባለላቸው ጊዜ እንኳን በትክክል ስለመጠናቀቃቸው ማስረጃ መቅረብ ባለመቻሉ የፌዴሬሽኑ መልስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑም ያስረዳል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲት መሥሪያ ቤት በክፍትነት ከጠቀሳቸው ከብዙ በጥቂቱ እንደተጠቀሰው ሆኖ፣ በተለይም ከዓለምና ከአህጉር አቀፍ ተቋማት ለቴክኒካል ዕርዳታ ለተቋሙ የሚላክለትን የቁሳቁስና የገንዘብ ዕርዳታ አስመልክቶ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋል አለመዋሉ መረዳት የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት ሊኖረው እንደሚገባ፣ የራሱን የገቢ ምንጭ ለማጎልበት መንቀሳቀስ እንዳለበትና ሌሎችም በርካታ በክፍተትነት የተመለከታቸውን በማመላከት ፌዴሬሽኑም ተቋማዊ ቅርፅ እንዲኖረው አስተያየቱን በመስጠት የ2008 ዓ.ም. የክዋኔ ኦዲት ሪፖርቱን አጠናቅሯል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ በበኩላቸው፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ያለፈው ዓመት የፌዴሬሽኑን ዕቅድ ክንውን ኦዲት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ ዓርብ ታኅሣሥ 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በፓርላማ ለመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ቀርበው በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ የሚሰጠቡት መሆኑን ጭምር ተናግረዋል፡፡

 

 

 

 

 

Standard (Image)

ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የወልዲያ ዘመናዊ ስታዲየም

$
0
0

አንድ ለእናቱ የነበረው የአዲስ አበባ ዓለም  አቀፍ ስታዲየም ከዓመታት ብቸኝነት ተላቆ በርካታ መሰሎቹን ለማየትና እርጅናውን የሚያሳብቁ ዘመናዊ ስታዲየሞችን ለመታዘብ በቅቷል፡፡

የወልዲያ፣ የባህር ዳርና የሐዋሳ ከተሞች በኢትዮጵያ አስገራሚ የተባሉ ስታዲየሞችን ገንብተው ዕውን አድርገዋል፡፡ ከእነዚህና በመገንባት ላይ ከሚገኙት ሌሎች የአገሪቱ ስታዲየሞች፣ በኢትዮጵያውያን ዕውቀትና የገንዘብ አቅም ግንባታው ተጠናቆ ጥር 6 ቀን 2009 ዓ.ም. በይፋ የሚመረቀው የወልዲያ ስታዲየም አንዱና የመጀመሪያው ያደርገዋል፡፡

ከዕድሜ ጠገቡ የአዲስ አበባ ስታዲየም ባሻገር ቦሌ አካባቢ የሚገነባው በአደይ አበባ ምስል የሚያሸበርቀው ብሔራዊ ስታዲየም፣ የወደፊት የእግር ኳሱ ድባብ ማራኪነት እንዲላበስ የሚያስችሉ ውጫዊ ገጽታ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከአዲስ አበባ በ520 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው የሰሜናዊቷ ወልዲያ ከተማ የተገነባው የሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ስታዲየም እስካሁን በአገሪቱ ከተገነቡት ለየት ያለ ዘመናዊ ይዘቶችን ያስተዋወቀ የስፖርት ማዕከል ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አረጋ ይርዳው የስታዲየሙን የምረቃ ሥነ ሥርዓት አስመልክቶ ባለፈው ረቡዕ ታኅሣሥ 12 ቀን 2009 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ከሆነ፣ ማዕከሉ ያረፈበት ቅጥር ግቢ በጠቅላላ የቆዳ ስፋቱ 177,000 ሜትር ካሬ ሲሆን፣ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) መሥፈርቶችን አሟልቶ ግንባታው የተጠናቀቀው ስታዲየም 25,155 ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ነው፡፡ ሙሉ የፀሐይ መጠለያና ዘመናዊ ልዩ መብራቶች (ፓውዛዎች) የተገጠሙለት ከመሆኑ ጎን ለጎን፣ በሜዳው ዙሪያ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) የሚጠይቀውን መመዘኛዎች የሚያሟላ በአንድ ጊዜ ስምንት ተወዳዳሪዎችን ማስተናገድ የሚችል የመሮጫ መም (ትራክ) ያለው ነው፡፡

በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ከስታዲየሙ በተጓዳኝ የኦሊምፒክ መመዘኛዎችን ያሟሉ ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ማለትም የእጅ ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ሜዳ ቴኒስና ሌሎችንም ከእንግዳ ማረፊያ ጋር አጣምሮ የያዘ ከመሆኑ ባሻገር የኦሊምፒክ ውድድሮችን ማስተናገድ የሚችል የመዋኛ ገንዳ ስፋቱ 25 X 50 ሜትር፣ ጥልቀቱ ደግሞ ከሁለት እስከ አምስት ሜትር የሚሸፍን እንደሆነ ጭምር የግንባታው የበላይ ተቆጣጣሪ ዶ/ር አረጋ ይርዳው አስረድተዋል፡፡

የስታዲየሙ ክብር ትሪቡን ሕንፃ ባለ ሦስት ፎቅ ሆኖ፣ በውስጡ አራት ቡድኖች በአንድ ጊዜ ሊያስተናግዱ የሚችሉ የልብስ መቀያየሪያ ክፍሎች፣ ሻወር፣ መፀዳጃ ቤቶች፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ የሕክምናና ሌሎችንም ተያያዥ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ክፍሎች የተሟሉለት ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ ሕንፃው የክብር እንግዶች ማረፊያና ማስተናገጃ፣ እንዲሁም ጨዋታዎችን በሬዲዮ ወይም በቴሌቪዥን ለማስተላለፍ የሚያስችሉ ስምንት ቻናሎችና የድምፅ መከላከያ ጭምር የተገጠመላቸው ስለመሆኑም በመግለጫው ተገልጿል፡፡

ስታዲየሙና ማዕከሉ ተወዳዳሪዎችን ከአደጋ ሊከላከል የሚችል ዘመናዊ አጥሮች ሲኖሩት፣ በተጨማሪም ስታዲየሙ ካሉት አሥር በሮች ሰባቱ በአደጋ ጊዜ አምቡላንሶችን ወደ ሜዳ ማስገባት የሚችሉ እንደሆኑም ተነግሯል፡፡

ሌላው ስለዚሁ የወልዲያ ዘመናዊ ስታዲየሞች የተነገረው በቅጥር ግቢው 308 የአውቶሞቢል፣ 14 የአውቶቡስና 16 የብስክሌት ማቆሚያ ቦታ ከተሟላ የትራፊክ ምልክቶች ጋር የተዘጋጀለት ከመሆኑ ጎን ለጎን፣ በስታዲየሙ ዙሪያ የተገጠሙ 156 ፓውዛዎች፣ የመብረቅ አደጋ መከላከያ፣ በዝናብ ጊዜ መጫወት እንዲያስችልና የሰረገን ውኃን ወደ ውጭ በመምጠጥ የሚያስተላልፍ ደረጃውን የጠበቀ የተፋሰስ ቦይ (ቱቦ) እንዲሁም የድምፅ ማጉያ፣ የውድድር ውጤት ማሳያ ኤሌክትሮኒክስ ማሳያዎች (ስኮር ቦርድ) እና የቴሌፎንና ኢንተርኔት አገልግሎት ሲስተም የተገጠመለት ስለመሆኑ ጭምር ዶ/ር አረጋ ገልጸዋል፡፡

የስታዲየሙና የማዕከሉ ግንባታዎች በአብዛኛው በአገር ውስጥ ምርቶችና በአገር በቀል ባለሙያዎች የተከናወነ መሆኑን ያከሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ግንባታው የወሰደው ጊዜ አራት ዓመት ተኩል ነው፡፡ የግንባታውን ሙሉ ወጭ የሸፈኑት ሼህ መሐመድ በአጠቃላይ 567,890,000 ወጪ ማድረጋቸው ተናግረዋል፡፡

የዘመናዊ ስታዲየም ባለቤት የሆነችውና በሰሜን ወሎ በየጁ የምትገኘው ወልዲያ፣ ከባህር ወለል 2,000 ጫማ ላይ ትገኛለች፡፡ በአሁኑ ወቅትም በፕሪሚየር ሊጉ እየተጫወተ የሚገኝ አንድ የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት ነች፡፡ ኅብረተሰቡም ከፍተኛ የእግር ኳስ ፍቅር ያለው ስለመሆኑም ይነገርለታል፡፡

በመጨረሻም የስታዲየሙ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ከሆነ በኋላ በባለቤትነት የሚያስተዳድረውን አካል አስመልክቶ ጥያቄ የቀረበላቸው ዶ/ር አረጋ፣ ንብረትነቱ የሼህ መሐመድ የሆነው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኃላፊነት ግንባታውን ካጠናቀቀ በኋላ እንደማይመለከተው ገልጸው፣ ንብረትነቱም የወልዲያ አስተዳደርና የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስታዲየሙ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን ማስተናገድ ይችል ዘንድ ከተቋማቱ ዕውቅና የሚያገኘው የአየር ንብረቱ ጭምር ግምት ውስጥ ገብቶ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደገለጹት፣ ሼህ መሐመድ የዚህን ስታዲየም ሙሉ ወጭ እንደሚሸፍኑ ማረጋገጫ ከሰጡ በኋላ የፊፋና የካፍን መስፈርት ግምት ውስጥ በማስገባት ሦስት ጊዜ የዲዛይን ማሻሻያ ሥራ ተደርጎለታል፡፡ ከዚህ በመነሳትም የኢትዮጵያ አየር እንደ ፋብሪካ ውጤቶች ታሽጎ (ፓክ) ተደርጎ የሚሸጥ ቢሆን ከየትኛውም አገር በተሻለ ተጠቃሚ ባደረገን ነበር ሲሉ የወልዲያን የአየር ንብረት ተስማሚነት አስረድተዋል፡፡

በአገሪቱ የወልዲያውን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ አስፈላጊነቱን አስመልክቶ ዶ/ር አረጋ፣ ‹‹መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ባለበት አገር ገና ተጀመረ እንጂ በቂ አይደለም፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡ አክለውም ከግማሽ በላይ የወጣት በሆነበት አገር ማዘውተሪያዎችን እንደየደረጃው በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች አስፋፍቶ ወጣቱን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጭምር ተናግረዋል፡፡

 

Standard (Image)

የ‹‹ማርሽ ቀያሪው›› ምሩፅ ይፍጠር ስንብት

$
0
0

ከሠላሳ ሰባት ዓመት በፊት የተካሄደው የሞስኮ ኦሊምፒክ ሲነሣ ቀድሞ የሚመጣው የሚወሳው ረዥም ርቀት ሯጩ ምሩፅ ይፍጠር ነው፡፡ የድል ቁርጠኝነት የተሞላበት አሯሯጡ የመላው ዓለምን ምናብ ሰንጎ መያዙ አይረሳም፡፡

በሞስኮ ኦሊምፒክ በሁለቱ ርቀቶች በ5,000 ሜተርና በ10,000 ሜትር ለተቀናቃኞቹ ዕድል ሳይሰጥ ተፈትልኮ የሮጠበትና ያሸነፈበት መንገድ ‹‹ይፍጠር ዘ ሺፍተር›› (ማርሽ ለዋጩ ምሩፅ - አካለ ማርሹ ምሩፅ) የተባለበትን ዳግም ያረጋገጠበት ነበር፡፡ በሞስኮ ድሉ ከተመሰጡና አርአያ ከሆነላቸው መካከል በወቅቱ የሰባት ዓመት ልጅ የነበረው ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ውድድሩን በትራንዚተር ሬዲዮ ጆሮውን ደቅኖ ሲከታተል አንድ ቀን የርሱን ዱካ እንደሚከተል አልሞ ነበር፡፡

ኢትዮጵያን የኦሊምፒክ ብርሃን ከዘጠና ሦስት ዓመት በፊት የዳሰሰው በፓሪስ ኦሊምፒክ አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኰንንና የክብር ተከታዮቻቸው በታደሙበት ቢሆንም፣ መወዳደር የጀመረችው ግን ከስድሳ ዓመት በፊት ሜልቦርን ላይ ነበር፡፡ የኦሊምፒክ የድል ጮራ የበራውም በሮም ኦሊምፒክ አበበ ቢቂላ በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ሲያጠልቅ ነው፡፡ ከአበበ ቢቂላ ጋር ማሞ ወልዴ፣ ምሩፅ ይፍጠር፣ ኃይሌ ገብረ ሥላሴና ቀነኒሳ በቀለ የኢትዮጵያ የምንጊዜም የረዥም ርቀት ዝነኞች ሆነው ተከስተዋል፡፡

ፋና ወጊው አበበ ቢቂላ የኦሊምፒክ ማራቶንን በ1952 ዓ.ም. (1960) እና 1957 ዓ.ም. (1964) ኦሊምፒኮች ድል ሲመታ፣ ምሩፅ ግን በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ ሁነኛ ሥፍራ ያሰጠውን አስደናቂ ድርብ ድል በሞስኮ በ1972 ዓ.ም. (1980) ተቀዳጅቷል፡፡

የሞስኮ ኦሊምፒክ የምሩፅ አስደናቂው ድርብ ድል እስከሚከሰትበት ድረስ የሚዲያ መድረኩን ተቆጣጥረውት የነበሩት ሁለት እንግሊዛውያን የ1,500 ሜትርና የ800 ሜትር ባለድሎቹ ሰባስቲያን ኮ እና ስቲቭ ኦቬት ነበሩ፡፡  በአስደናቂ አሯሯጡና በልዩ ችሎታው ማርሽ ቀይሮ ያሳየው ብልጫ ሩጫውን ሕይወት ሰጠው፡፡ ሐምሌ 22 ቀን 1972 ዓ.ም. በተካሄደው የ10 ሺሕ ፍጻሜ ከምሩፅ ይፍጠር ጋር አብረው የተሰለፉ መሐመድ ከድርና ቶሎሳ ቆቱ በሁለት ኦሊምፒክ የበላይ የነበረችው ፊንላንድ በሻምፒዮኑ ላሲ ሸረን መሪነት ካርሎ ማኒንካን ይዞ የታየው የ25 ዙር ታክቲካዊ ትግል የተቋጨው፣ ውድድሩ ሊያበቃ 300 ሜትር ሲቀረው ምልዓተ ኃይሉን ተጠቅሞ ባፈተለከው ምሩፅ ይፍጠር ድል አድራጊነት ነበር፡፡ ምሩፅ የመጨረሻውን 200 ሜትር በ26.8 ሰከንድ በመሮጥ መስመሩን በጥሶ ያለፈው በ27 ደቂቃ 42.69 ሰከንድ ነበር፡፡ ማኒንካ ብር፣ መሐመድ ነሐስ ሲያገኙ ቶሎሳና ቬረን ተከታዮቹን ቦታ ይዘው ፈጽመዋል፡፡

ይህ በሁለቱ በኢትዮጵያና በፊንላንድ መካከል የነበረውን ፉክክር ለማየት በወቅቱ የፊንላንድ ፕሬዚዳንት የነበሩት በስፍራው መገኘታቸው ይታወሳል፡፡ በ5,000 ሜትርም ምሩፅ የመጨረሻውን 200 ሜትር በ27.2 ሰከንድ በማለፍ ድሉን ያጣጣመው በ13፡20.91 ሲሆን፣ ያስከተላቸውም ታንዛኒያውን ሱሌይማን ንያምቡና ፊንላንዳዊውን ማኒካን ነበር፡፡

ምሩፅ ስለ ሞስኮ ድሉ ከ12 ዓመት በፊት ላናገረው የኢንተርናሽናል አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር ድረ ገጽ እንዳወጋው፣ ያኔ ከአሠልጣኞቻቸው ጋር የተነጋገሩት ርሱም የተለማመደው በሁለቱም ርቀቶች 300 ሜትር ሲቀር አፈትልኮ ለመሮጥ ነበር፡፡ ‹‹አምስት ዙር እንደቀረው የተቀናቃኞቼን እንቅስቃሴና ትርታ ማዳመጥ ጀመርሁ፤  ውጥረት የሚሰፍነው ደወሉ ሲደወል በመሆኑና አቅማቸውን አሰባስበው ከመነሳታቸው በፊት 300 ሜትር ሲቀር ማምለጥ እንዳለብኝ ወሰንሁ፤ ድሉንም ጨበጥኩ፡፡›› 

የምሩፅ ይፍጠር የሩጫ ጉዞ

መስከረም 1961 ዓ.ም. አበበ ቢቂላና ማሞ ወልዴን የያዘው የሜክሲኮ ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ ተሳታፊ አትሌቶች የመጨረሻ ጉዟቸውን ወደ ሜክሲኮ ሲቲ ከማድረጋቸው በፊት ለልምምድ ያረፉት አስመራ ከተማ ነበር፡፡ በአስመራ ንግሥተ ሳባ ስታዲየም ልምምድ ሲያደርጉ የተመለከተው የከተማዋ ነዋሪ ምሩፅ ይፍጠር ለወደፊት ሕይወቱ በር ከፋች አጋጣሚ ፈጠረለት፡፡ በልምምድ ሩጫ ውድድርም ከነማሞ ወልዴ ጋር ተወዳድሮ መጨረሻ ቢወጣም አሯሯጡንና አቅሙን ያስተዋሉት አሠልጣኝ ንጉሤ ሮባ በአየር ኃይል ስፖርት መምሪያ እንዲያዝና ልምምድ እንዲያደርግ አደረጉ፡፡ ቅጥሩንም ፈጸመ፡፡ ለ20 ዓመታት በአየር ኃይል ሲያገለግል እስከ ሻምበልነት ደርሷል፡፡

በአዲስ አበባው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስታዲየም፣ ንብ የሚባለውን የአየር ኃይል ስፖርት ክለብን እየወከለ በብሔራዊ ሻምፒዮናና በጦር ኃይሎች ውድድር ውጤታማ መሆን የጀመረው ምሩፅ፣ የመጀመሪያው ኢንተርናሽናል ውድድሩ በ1962 ዓ.ም. በምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታንዛኒያ ውስጥ በ1,500 ሜትር ከኦሊምፒክ ባለወርቁ ኬፕቾግ ኬይኖ ጋር ተወዳድሮ ሦስተኛ የወጣበት ውድድሩ ነበር፡፡

በ1963 ዓ.ም. በአሜሪካ በተካሄደው የአፍሮ አሜሪካን ውድድር በ10 ሺሕ ወርቅ፣ በ5 ሺሕ ሜትር ብር ሜዳሊያ በማግኘት ድሉን አሐዱ ብሎ ጀምሯል፡፡

የመጀመሪያው የኦሊምፒክ መድረኩ በሆነው 20ኛው ኦሊምፒያድ በሙኒክ ሲካሄድ ምሩፅ በ5 ሺሕና በ10 ሺሕ ሜትር ለመወዳደር ነበር ወደ ሥፍራው ያመራው፡፡ በ10 ሺሕ ሜትር በማጣሪያው አንደኛ ወጥቶ በፍጻሜው ሦስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያን አግኝቷል፡፡ በ5 ሺሕ ሜትር ማጣሪያ ‹‹አሠልጣኞቹ በፈጠሩት ችግር›› ምክንያት በጊዜ ባለመድረሱ የተነሳ ሳይወዳደር በመቅረቱ ሌላ ሜዳሊያ የማግኘት ዕድሉ ተጨናግፎበታል፡፡

በ1965 ዓ.ም. በሌጎስ (ናይጄሪያ) በተካሄደው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች በ10 ሺሕ ወርቅ በ5 ሺሕ ብር አሸንፏል፡፡ በዚያው ዓመት ከሁሉም የስፖርት ዓይነቶች ከተውጣጡት መካከል የኢትዮጵያ ስፖርት ኮከብ አትሌት ተብሎ የተመረጠው ምሩፅ፣ በ1968 ዓ.ም. በሞንትሪያል (ካናዳ) በተካሄደው 21ኛው ኦሊምፒያድ ያለ ጥርጥር በ5,000 እና በ10,000 ሜትር ሁለት ወርቅ ያገኛል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ስፖርታዊ ግንኙነት የነበራት ኒውዚላንድ ከሞንትሪያል ኦሊምፒክ ባለመታገዷ ምክንያት አፍሪካውያን አንካፈልም በማለታቸው ሳይወዳደር ተመልሷል፡፡

በሙኒክ ኦሊምፒክ ምሩፅን ያሸነፈው ፊንላንዳዊው ላሲ ቨረን ዳግመኛ ድሉን ምሩፅ በሌለበት አጣጣመ፡፡

ምሩፅ የኦሊምፒክ ወርቅ ሕልሙን ያሳካው በ1972 ዓ.ም. ሞስኮ ባስተናገደችው 22ኛ ኦሊምፒያድ ሲሆን በሁለቱም ርቀቶች ወርቁን ያጠለቀው ፊንላንዳዊውን ላሲ ቨረንን ድል በመምታት ነበር፡፡

በሞስኮ ኦሊምፒክ ሲሮጥ ዕድሜው የገፋው (በፓስፖርት ዕድሜው 36 ዓመቱ በተለያዩ ሚዲያዎች እስከ 42 የሚያደርሱት) ምሩፅ፣ በ1969 ዓ.ም. እና በ1971 ዓ.ም. በተካሄዱት የዓለም አትሌቲክስ ዋንጫዎች አፍሪካን በመወከል አራት ወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ ተወዳዳሪዎቹን በቀደመበት ርቀት ያህል በሞስኮ አልደገመውም፡፡ ዕድሜው ገፍቷልና፡፡

በሁለቱ የዓለም ዋንጫዎች በ5,000 ሜትር ውድድሩ ሊያበቃ 500 ሜትር ሲቀር፣ በ10 ሺሕ 600 ሜትር ሲቀር ነበር ማርሽ ቀይሮ በማፈትለክ ያሸነፈው፡፡ በሞስኮ ኦሊምፒክ ግን በሁለቱ ርቀቶች እንደ ቅደም ተከተላቸው 200 ሜትርና 300 ሜትር ሲቀረው ነበር፣ ማርሽ ቀይሮ ድል የመታው፡፡ ምሩፅ በ1971 ዓ.ም. በዓለም ዋንጫ አፍሪካን ወክሎ ለመካፈል የበቃው የመጀመሪያው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዳካር (ሴኔጋል) ሲካሄድ ሁለት ወርቅ (በ5 ሺሕና 10 ሺሕ) በማግኘቱ ነበር፡፡

ምሩፅ 1971 ዓ.ም. ወርቃማ ዓመቱ ነበር፡፡ እጅግ የገነነበት ታላቅ ክብርንም የተቀዳጀበት፡፡ በዚያው ዓመት በቼኮዝሎቫኪያ በተዘጋጀው የዓለም ኮከብ አትሌቶች ምርጫ ዘጠኝ አትሌቶች ሲመረጡ አንዱ ምሩፅ ሲሆን፣ ‹‹የኮከቦች ኮከብ›› ተብሎ መመረጡ በተዘጋጀው የተሸላሚዎች መድረክ ራሱ ከመሀል በከፍታ መቀመጡ ይታወሳል፡፡ የወርቅ ጫማም ተሸላሚ ነበር፡፡ ምሩፅ ድርብ ድሎቹን በዳካር፣ በሞስኮና ሞንትሪያል በተደረጉ አህጉራዊና ዓለማዊ ውድድሮች ስድስት ወርቅ ይዞ አዲስ አበባ በደረሰ ጊዜ ጋዜጠኛ ኃይሉ ልመንህ እንዲህ ገጥሞለት ነበር፡፡

‹‹አብዮቱ ፈካ አበባው አማረ

ያለም ሻምፒዮና በምሩፅ ሠመረ፡፡

ሞስኮ ላይ ቀደመ ዳካር ላይ ድል መታ

ሞንትሪያል ደገመ እንዳመሉ ረታ

ዓለም ይሁን አለ ድሉን ተቀበለ

እየደጋገመ ምሩፅ ምሩፅ አለ፡፡››

የመጀመሪያ ዓለም ዋንጫ በዱዞልዶርፍ (ምዕራብ ጀርመን) ሲካሄድ አፍሪካን ወክሎ ለመሳተፍ የበቃው የቅርብ ተቀናቃኙን ኬንያዊውን የዓለም ሪከርድ ባለቤት ሔንሪ ሮኖን በመርታት ነበር፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት (በወቅቱ ኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ) ሻምበል ምሩፅ በቅድመ ሞስኮ ኦሊምፒክ ባገኛቸው አህጉራዊና ኢንተርናሽናል ድሎች ኢትዮጵያን ለታላቅ ግርማ ሞገስ በማብቃት ለፈጸመው አኩሪ ተግባር አምስተኛው የአብዮት በዓል ሲከበር፣ ‹‹የጥቁር ዓባይ ኒሻን››ን ከርዕሰ ብሔሩ ሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እጅ መቀበሉ ይታወሳል፡፡

በ1,500 ሜትር መወዳደር የጀመረው ምሩፅ 5 ሺሕና 10 ሺሕ መደበኛ ውድድሮቹ ቢሆኑም በጎዳና ላይ ሩጫዎችም ተደጋጋሚ ድሎች ማግኘቱ አይሳትም፡፡

በተለይ በተከታታይ ዓመታት ድል የተጎናፀፈበት የፖርቶ ሪኮ ግማሽ ማራቶን ውድድር ለዓለም ክብረ ወሰን የበቃበት ነበር፡፡ ጥር 29 ቀን 1969 ዓ.ም. በፖርቶ ሪኮ ኮዓሞ የ21 ኪሎ ሜትር (ግማሽ ማራቶን) ውድድር ምሩፅና መሐመድ ከድር ተከታትለው ሲያሸንፉ ምሩፅ የገባበት 1 ሰዓት 02 ደቂቃ 57 ሰከንድ ያለም ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቦለታል፡፡

በ1972 በፖርቶ ሪኮ ግማሽ ማራቶን አሸንፎ እንደተመለሰ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫም ‹‹የማተኩረው በሞስኮ ኦሊምፒክ ስለሆነ በፖርቶ ሪኮው ድሌ አልኮራም›› ማለቱ አይዘነጋም፡፡

በሞስኮ ኦሊምፒክ ለሦስተኛ ጊዜ ድሉን ለማጣጣም ቋምጦ የነበረው ፊንላንዳዊ ላሲ ቬረን በሞስኮ አየሩ ጥሩ ከሆነ እንደሚያሸንፍ መናገሩን ተከትሎ ምሩፅ በሰጠው አፀፋ ‹‹ሐሩርም ይሁን በረዶ እኔ ከማሸነፍ የሚገታኝ አንዳች ኃይል የለም›› ማለቱ ልበ ሙሉነቱን ያሳየበት አጋጣሚ ነበር፡፡

ከሞስኮ ኦሊምፒክ ድሉ በኋላ ጥንታዊ ኦሊምፒክ በተመሠረተባት ግሪክ ለኦሊምፒያዊ ሽልማት ከተመረጡ አምስት አትሌቶች ቀዳሚ ሆኖ የኦሊምፒክ ሎሬት አክሊልን ከርዕሰ ብሔሩ የተቀበለው ምሩፅ ይፍጠር ነበር፡፡

በዓለም ገናና ለሆነው ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ ለሞሮኮው ሰዒድ አዊታና ለሌሎችም አርአያ የሆነው ምሩፅ፣ ኢንተርናሽናል አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር በ1973 ዓ.ም. በምዕራብ ጀርመን ባደን ባደን ጉባኤውን ሲያካሂድ የዓለም አትሌቶችን ከወከሉ አትሌቶች አንዱ ርሱ ነበር፡፡ ሌላኛው ተወካይ እንግሊዛዊው ያሁኑ የኢንተርናሽናል አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር ፕሬዚዳንት የያኔው የሞስኮ ኦሊምፒክ የ1,500 ሜትር ባለድል ሰባስቲያን ኮ ነበር፡፡

ጀንበሯ ስትጠልቅ

ከሁለት አሠርታት ወዲህ በአብዛኛው መቀመጫውን በካናዳ አድርጎ የነበረው ምሩፅ፣ ከዓመት ወዲህ ባደረበት ጽኑ የሳምባ ሕመም ምክንያት ሕክምናውን እየተከታተለ ቢቆይም፣ ከሐሙስ ታኅሣስ 13 ቀን 2009 ዓ.ም. ወዲህ መሻገር አልቻለም፡፡ በቶሮንቶ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ሕይወቱ ማለፉ በካናዳ ለቤተሰቡ ቅርብ የሆነው አድናቂና ወዳጁ አቶ ታምሩ ተስፋዬ በስልክ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ዜና ዕረፍቱን ተከትሎ ቤተሰቡ በካናዳ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲሁም ጥልቅ ሐዘናቸውን ከገለጹት ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር መገናኘቱንና አስክሬኑን በክብር ወደ አገሩ ለመመለስ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

‹‹ምሩፅ አገሬ ወስዳችሁ ነው የምትቀብሩኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለውለታዬ ነው›› ይል እንደነበረ ያስታወሱት አቶ ታምሩ፣ በገና በዓል ምክንያት መሥሪያ ቤቶች ዝግ በመሆናቸው ሒደቱን ማፋጠን ባለመቻሉ ሰነዶቹ ተሟልተው እንዳበቁ በቀናት ውስጥ አስክሬኑ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓጓዝ ተናግረዋል፡፡

የሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ሥርዓተ ቀብር በክብር ለማስፈጸም በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የተሰየመ ኮሚቴ መኖሩንና የብሔራዊ  አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መሪዎች ኃይሌ ገብረሥላሴና ገብረ እግዚአብሔር እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በአዲስ አበባ የሚገኘው ልጁ ቢንያም ምሩፅ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስክሬኑን ለማጓጓዝ መጠየቁን ያወሳው ቢንያም፣ ለምሩፅ የጀግና ሽኝት እንደሚደረግለት እምነቱ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ያ ስመ ገናና ‹‹ይፍጠር ዘ ሺፍተር››፣ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ ከካናዳ ሆኖ በባዕድ መንግሥት እየታገዘ በነበረበት ሰዓት ምሩፅ፣ እጅግ ውድና በገንዘብ የማይተመኑት ሽልማቶቹ በጨረታ ተሸጠው ለሕክምና እንዲውሉ ሲጠየቅ ‹‹ሽልማቶቼ የኢትዮጵያ ሕዝብ ናቸው፤ ለሽያጭ አይታሰቡም›› ማለቱ አይዘነጋም፡፡

ከአባቱ አቶ ይፍጠር ተክለሃይማትና ከእናቱ ወ/ሮ ለተገብርኤል ገብረአረጋዊ ጥቅምት 5 ቀን 1937 ዓ.ም. በትግራይ፣ ዓዲግራት የተወለደውና በ72 ዓመቱ ያረፈው ምሩፅ ይፍጠር የሰባት ልጆች አባት ነበር፡፡

የምሩፅ ይፍጠር ዓበይት ድሎች

ኢትዮጵያን በመወከል

ሜዳሊያ

እ.ኤ.አ.

ኦሊምፒክ ጨዋታዎች

ወርቅ

1980

ሞስኮ

5,000 ሜትር

ወርቅ

1980

ሞስኮ

10,000 ሜትር

ነሐሰ

1972

ሙኒክ

10,000 ሜትር

መላ አፍሪካ ጨዋታዎች

ወርቅ

1973

ሌጎስ

10,000 ሜትር

ብር

1973

ሌጎስ

5,000 ሜትር

አፍሪካን በመወከል

የአይኤኤፍ ዓለም ዋንጫ (የዓለም አትሌቲክስ ዋንጫ)

ወርቅ

1977

ዱዘልዶርፍ

5,000 ሜትር

ወርቅ

1977

ዱዘልዶርፍ

10,000 ሜትር

ወርቅ

1979

ሞንትሪያል

5,000 ሜትር

ወርቅ

1979

ሞንትሪያል

10,000 ሜትር

 

         

 

Standard (Image)

እግር ኳስ ፌዴሬሽን በታዳጊ ወጣቶችና በሀብት አጠቃቀም ጉዳይ ትኩረት እንዲያደርግ ተጠየቀ

$
0
0

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እግር ኳሱን በመላ አገሪቱ በማስፋፋት ረገድ የተሻለ እንቅስቃሴ ቢኖረውም፣ ታዳጊ ወጣቶች ላይ ግን ኅብረተሰቡና መንግሥት በሚፈልጉት መጠን አለመሠራቱ በፓርላማው የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ግምገማ አመለከተ፡፡ ለቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ እንዲሰጡ ከተገኙት የፌደሬሽኑ አመራሮች አንዳንዶቹ ፌዴሬሽኑም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ለታዳጊ ወጣቶች የሚሰጡት ትኩረት አነስተኛ እንደሆነም መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ እግር ኳሱን ለመምራትና ለማስፋፋት እያከናወነ ያለውን የአሠራር ሥርዓት በተመለከተ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ባቀረበው የክዋኔ ሪፖርት ላይ በፓርላማው ለመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዓርብ ታኅሣሥ 14 ቀን 2009 ዓ.ም. ፌዴሬሽኑ ቀርቦ ማብራሪያ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡

በፌዴራሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የክዋኔ ሪፖርት መሠረት ግምገማውን ያደረገው ቋሚ ኮሚቴው፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እግር ኳሱን በመላ አገሪቱ ለማስፋፋት እያደረገ ያለውን የሊግ አደረጃጀት አድንቆ፣ ተተኪና ታዳጊ ወጣቶችን የተመለከተ ግን አጥጋቢና ሊታይ የሚችል እንቅስቃሴ እያደረገ አለመሆኑ በክፍተትነት ታምኖበታል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከተቋቋመለት ዓላማ አኳያ፣ ከሁሉ በፊት የአገሪቱ እግር ኳስ አስታማማኝ መሠረት ኖሮት ይቀጥል ዘንድ በተለያየ የዕድሜ ደረጃ ተከፋፍለው ሊንቀሳቀሱ የሚችሉ የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት የለውም፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ደግሞ እግር ኳሱና ኅብረተሰቡ የሚፈልገውን ውጤት ማሳካት እንደማይችል ጭምር በቋሚ ኮሚቴው ለፌዴሬሽኑ መገለጹ ታውቋል፡፡

የታዳጊ ወጣቶችን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ፌዴሬሽኑ ባቋቋመው ቴክኒክና ልማት ዲፓርትመንት አማካይነት ሁሌም ሲነገር የሚሰማው በአገሪቱ በታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት የታቀፉ 5,000 ታዳጊ ወጣቶች እንዳሉ ነው፡፡ ይሁንና በቋሚ ኮሚቴው እንደተጠቆመው ሁሉ፣ ፌዴሬሽኑ ወረቀት ላይ ያለውን ወደ ጎን በመተው በምትኩ እውነታው ወደ መሬት ማውረድ የሚችሉ ሙያተኞች በመያዝ ለእግር ኳሱ የወደፊት ህልውና መንቀሳቀስ እንደሚገባ ነው ብዙዎች ሲናገሩ የሚደመጠው፡፡

ሌላው በፓርላማው የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በክፍተትነት የታየው፣ ፌዴሬሽኑ ከፊፋም ሆነ ከመንግሥት የሚያገኘውን የገንዘብና የቁሳቁስ ድጎማ ተጠያቂነትና ግልጽነት በተሞላበት አግባብ መጠቀም እንዳለበትም አቅጣጫ ተቀምጦለታል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የዓመቱ ውድድሮች በወጣላቸው መርሐ ግብር መሠረት ተጀምረው በወቅቱና በጊዜው እንደማይጠናቀቁ፣ ይህ ደግሞ ክለቦችንና ሌሎች የመንግሥት ተቋማትን ተገቢ ላልሆነ ወጪ የሚዳርጋቸው ስለመሆኑም  በክፍተትነት ተወስዷል፡፡

በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ሙሉ ወጪ ግንባታው ከተጀመረ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረው በአዲስ አበባ ሲኤምሲ አካባቢ የሚገኘው የምሥራቅ አፍሪካ እግር ኳስ አካዴሚ ጉዳይም በቋሚ ኮሚቴው ቅሬታ ከቀረበባቸው መካከል አንዱ እንደነበረም ተመልክቷል፡፡ 

Standard (Image)

አቶ ዱቤ ጂሎ ወደ ቀድሞ ኃላፊነታቸው ተመለሱ

$
0
0

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለሁለት አሠርታት ያህል በተለያየ የኃላፊነት ቦታ ሲያገለግሉ ቆይተው በራሳቸው ጥያቄ ከኃላፊነታቸው መለቀቃቸው የተነገረላቸው አቶ ዱቤ ጂሎ፣ በኃላፊነት እንደ ገና ወደ ፌዴሬሽኑ መመለሳቸው ታወቀ፡፡ በመሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥ (ቢፒአር) ጥናት መሠረት በቀድሞ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተዋቀሩ ሦስት ዲፓርትመንቶችን በአስተባባሪነት እንዲመሩ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋልም ተብሏል፡፡

ሕጋዊ የሕግ ማዕቀፍ ኖሯቸው በአገሪቱ ከተደራጁ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ለበርካታ ዓመታት በአሠራርና በአደረጃጀት ወቀሳና ትችት ከሚቀርብባቸው መካከል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህንኑ መነሻ በማድረግ የቀድሞ የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥ ጥናት በማድረግ ተቋሙ እንደገና አዳዲስ ዲፓርትመንቶች ተካተውበት እንዲደራጅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ቀድሞ ቴክኒክና ልማት ተብሎ በአንድ ዲፓርትመንት በአቶ ዱቤ ጂሎ ኃላፊነት ይመራ የነበረው ክፍል፣ ለሦስት በመክፈል ውድድርና ተሳትፎ፣ ሥልጠና ምርምርና ጥናት እንዲሁም የውጭ ጉዞ ፋሲሊቲና ማኅበራት ማደራጃ በሚል የየራሳቸው ኃላፊዎች እንዲኖራቸው ተደርጎ እንዲዋቀሩ ተደርጓል፡፡ በተመሳሳይ በአንድ ዳይሬክተር ተጠቃሎ ሲተዳደር የቆየው አስተዳደርና ፋይናንስም እንደዚሁ ተከፋፍሎ እንዲደራጀ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በጊዜው መሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥ ‹‹ያስፈልጋል? አያስፈልግም?› በሚል በፌዴሬሽኑ መካከል አለመግባባቶች ይደመጡም ነበር፡፡

የአገልግሎት ዘመኑ ሊጠናቀቅ በመጨረሻዎቹ ወራት ይገኝ የነበረው የቀድሞ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ ጥናቱን መሠረት በማድረግ የየዲፓርትመንቱን ኃላፊዎች ምደባና ቅጥር እያከናወነ በሚገኝበት በጥር 2008 ዓ.ም.፣ የቀድሞው የፌዴሬሽኑ ቴክኒክና ልማት ዲፓርትመንት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ዱቤ ጂሎ የሥራ መልቀቂያ አስገብተው መልቀቃቸው ይታወቃል፡፡ ይሁንና የአትሌቲክሱን ውጤት መነሻ ያደረገ አለመግባባት በቀድሞ አትሌቶችና በፌዴሬሽኑ መካካል እንዲፈጠር ምክንያት ሆነ፡፡ አለመግባባቱ ቀስ በቀስ ‹‹የፌዴሬሽኑ የኃላፊነት ቦታ ይገባናል›› በሚለው የቀድሞ አትሌቶች ጥያቄ አሸናፊነት ተደምድሞ፣ መስከረም 2009 ዓ.ም. መጨረሻ በተደረገው የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሆኖ መመረጡ ይታወሳል፡፡

የፌዴሬሽኑ አዲሱ አመራር ኃላፊነቱን ተረክቦ እየተንቀሳቀሰ እስከሚገኝበትና ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ተቋሙ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫም የለም፡፡ ይሁንና በፌዴሬሽኑ ያለውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ምንጮች ለሪፖርተር እንደሚገልጹት ከሆነ፣ ዲፓርትመንቶችን በተለይም ቴክኒካዊ ክፍሎችን በሚመሩ ሙያተኞችና በሥራ አስፈጻሚው መካከል አለመግባባቶች እንዳሉ ነው፡፡

እንደምንጮቹ ከሆነ፣ በሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ የሚመራው አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተቋሙ ቴክኒካዊ በሆኑ አሠራሮች ላይ በመልካም ፈቃደኝነት የሚሠሩ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከብሔራዊ የወጣቶች አካዴሚና ከቀድሞ አትሌቶች ሁለት ሁለት በድምሩ 12 ሙያተኞች በአማካሪ ቦርድ ስም ተዋቅረው፣ ተጠሪነታቸው ደግሞ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚው ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ የሚል ሐሳብ በመያዝ ጉዳዩን ሦስቱ ማለትም የውድድርና ተሳትፎ፣ የሥልጠና ጥናትና ምርምርና የውጭ ጉዞ ፋሲሊቲና ማኅበራት ማደራጃ ዲፓርትመንቶች እንዲመክሩበት ይደረጋል፡፡ የዲፓርትመንቶቹ አመራሮች ‹‹አማካሪ ቦርዱ›› ተጠሪነቱ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መሆን እንደሌለበትና ምርጫውም በማስታወቂያ መሆን እንደሚገባው ሐሳብ በማቅረባቸው ምክንያት የአማካሪ ቦርዱ መዋቅር እንዲሰረዝ መደረጉ ጭምር እነዚሁ ምንጮች ይናገራሉ፡፡

በፌዴሬሽኑ በአዲሱ ምርጫ የደቡብ ክልልን ወክለው ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የተመረጡት በአቶ አድማሱ ሳጂ ሲመራ የቆየው የሥልጠና ጥናትና ምርምር ዲፓርትመንት ይመራ የነበረው በተጠባባቂ ኃላፊ ነበር፡፡ ሆኖም ባለመግባባቱ ምክንያት እንዲቀር በተደረገው አማካሪ ቦርድ ምትክ አቶ ዱቤ ጂሎ እንዲወዳደሩ ተደርጎ የሥልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ተደርገው ስለመመደባቸው ተነግሯል፡፡ በተጨማሪነትም በመሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጡ ምክንያት ተጠሪነታቸው ለፌዴሬሽኑ ዋና ጸሐፊ የነበሩት ሦስቱ ዲፓርትመንቶች ከጽሕፈት ቤቱ ተለይተው አቶ ዱቤ ጂሎ እንዲቆጣጠሯቸው መደረጉንም ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

Standard (Image)

ለገድለኛው ሯጭ ምሩፅ ይፍጠር በቶሮንቶ ጸሎተ ፍትሐት ተደረገለት

$
0
0

ለገድለኛው (ሌጀንድ) ኢትዮጵያዊ ሯጭ ምሩፅ ይፍጠር፣ ባረፈበት የካናዳዋ ቶሮንቶ ከተማ፣ ትናንት ማክሰኞ ታኅሣሥ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ጸሎተ ፍትሐት ተደረገለት፡፡ ‹‹ይፍጠር ዘሺፍተር›› (ማርሽ ቀያሪው ምሩፅ ይፍጠር)፣ ‹‹ይፍጠር ዘማስተር›› (የሩጫ ጌታው ምሩፅ ይፍጠር) በመባል የዐቢይ አድናቆት ባለቤት ለነበረው ምሩፅ ይፍጠር ጸሎተ ፍትሐቱ የተደረገው፣ በቶሮንቶ በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን ሲቢሲ ኒውስ በድረ ገጹ ዘግቧል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ካህናትና ምዕመናን መገኘታቸው ታውቋል፡፡ በ1972 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1980) በሞስኮ ኦሊምፒክ ሁለት ወርቆችን በ10ሺሕና በ5ሺሕ ሜትር፣ በ1964 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1972) በሙኒክ ኦሊምፒክ በ10ሺሕ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ ያሸነፈው ምሩፅ ይፍጠር በሳምባ ጽኑ በሽታ በ72 ዓመቱ ያረፈው ታኅሣሥ 13 ቀን 2009 ዓ.ም. መሆኑ ይታወሳል፡፡ የኦሊምፒክ ሻምፒዮኑ ምሩፅ አስክሬን፣ በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ እንደሚገባና ሥርዓተ ቀብሩም ከተለያዩ አካላት ተውጣጥቶ በተቋቋመው ኮሚቴ አማካይነት በክብር እንደሚፈጸም ይጠበቃል፡፡ በዐሥራ ሦስት ዓመታት የሩጫ ሕይወቱ ከመካከለኛ ርቀት ማለትም ከ1,500 ሜትር እስከ ረዥም ርቀት (5,000 እና 10,000 ሜትር)፣ እንዲሁም ግማሽ ማራቶንን ጨምሮ ባሉት ርቀቶች በመወዳደርና ከ250 በላይ ተሳትፎ በማድረግ በአንደኛነት ያጠናቀቀው ምሩፅ ይፍጠር፣ ከኦሊምፒክ ድርብ ድሎቹ በተጨማሪ አህጉሮች በሚካፈሉበት የዓለም አትሌቲክስ ዋንጫ በ1969 እና በ1971 ዓ.ም. በ5,000 እና በ10,000 ሜትር ለአፍሪካ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎች ማስገኘቱ ይታወቃል፡፡ 

Standard (Image)

የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ደንብና መመርያ የሕገ መንግሥታዊነት ጥያቄ አስነሳ

$
0
0

ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች ለማስመዝገብ ያቀደቻቸውን ሁሉን አቀፍ ዕድገት በአጭር ጊዜ ለማሳካት ከተደቀኑባት ተግዳሮቶች መካከል የበቁ ባለሙያዎች እጥረት አንዱ እንደሆነ የተባበሩት መንግሥታት እንዲሁም የዓለም ባንክ ያወጧቸው ሰሞነኛ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡ ለዚህም ነው ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የበቁና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን ማሳተፍ የሚያስችላትን የዳያስፖራ ተሳትፎ ስትራቴጂ ነድፋ በመንቀሳቀስ ላይ የምትገኘው፡፡ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ከተካተቱት ቁልፍ ተግባራት መካከል የአገሪቱ የስፖርት ልማት አጀንዳ አንዱ ነው፡፡ ይህ በስፖርት ዘርፍ በአገሪቱ የሚታየውን የክህሎትና የዕውቀት እንዲሁም የሙያ ክፍተት ለመሙላት አስተዋጽኦ ታሳቢ በማድረግ የተዘረጋ የዕቅድ ሰንሰለት መሆኑም ታሳቢ ሊደረግ እንደሚገባ የሚናገሩ አሉ፡፡

የስፖርት ልማት በተለይ እግር ኳስና አትሌቲክስ ከፍተኛ አገራዊ መግባባትን በመፍጠርና ገጽታን በማስተዋወቅ እንዲሁም ገቢ በማስገኘት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለስኬቱም በሙያው ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው የአገር ውስጥና የውጭ ባለሙያዎችን በማሳተፍ ከፍተኛ ንቅናቄ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን የተለያዩ የስፖርት ጥናቶች በተደጋጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

ይህን አገራዊ የተሳትፎና የዕድገት መሠረታዊ እሳቤ ወደ ጎን በመተው የተለያዩ የስፖርት አደረጃጀቶች በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ተሳትፎ ገሸሽ የሚያደርጉ ወይም የሚገድቡ ውስጠ ደንቦችን በማውጣት ለስፖርቱ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊደረግ የሚችልበትን ዕድል በመንፈግ ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስጠ ደንቦች አንዳንዶቹን ለዚህ በማሳያነት በመጥቀስ የሚተቹ አሉ፡፡ በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት አሜሪካዊ የሆኑት የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ አቶ ዮሐንስ ሳሕሌ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በሚመለከት በአዋጅ ቁጥር 1/1987 ዓ.ም. በወጣው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ ሥራ ላይ የሚውሉ ማንኛውም ሕጎችም ሆነ ደንቦች ከሕገ መንግሥቱ ጋር መጋጨት ወይም መቃረን የሌለባቸው እንደሆነ የደነገገውን በመጥቀስ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሚጠቀምባቸው አንዳንዶቹ ውስጠ ደንቦች ከአገሪቱ ሕግ ጋር ተጣጥመው እንዲወጡና ሥራ ላይ እንዲውሉ ከሚጠይቁት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

እንደ አቶ ዮሐንስ ከሆነ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ ላይ በዋለው መተዳደሪያ ደንብ በአንቀጽ 30 በሰፈረው የብሔራዊ ፌዴሬሽኑን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የመምረጫ መመዘኛዎች ውስጥ ከተዘረዘሩት አንዱ፣ ከአገሪቱ መደበኛ ሕጎች ጋር የሚጋጭ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ ይኼውም የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ለመሆን በዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆነ በሚል የተቀመጠው ይህ አንቀጽ ለአገሪቱ ስፖርት ዕድገት ሊጠቅሙ የሚችሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ አያካትትም ይላሉ፡፡

በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ሥራ ላይ በዋለው አዋጅ ቁጥር 270/1994 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ተወላጅ ሆነው የውጭ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣ ከመሆኑ ጎን ለጎን የተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በማንኛውም የስፖርት ዓይነት በሥራ አስፈጻሚ አመራርም ሆነ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ እንዳይሳተፉ እንደማይከለክል በመጥቀስ አቶ ዮሐንስ ያምናሉ፡፡

በዚህ የኢትዮጵያ ተወላጆች በሚለው አዋጅ ውስጥ በአንቀጽ 6 በተገለጸው  ማለትም በማናቸውም በመንግሥት ደረጃ በሚካሄድ ምርጫ የመምረጥና የመመረጥ መብት እንደሌላቸው፣ በማንኛውም የአገር መከላከያ፣ የአገር ደኅንነት ወይም በውጭ ጉዳይ መሰል የፖለቲካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በመደበኛነት መሥራት የማይችሉ መሆኑ መደንገጉን ያስረዳሉ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መተዳደሪያ ደንብ ግን ይህንን አዋጅ በሚቃረን መልኩ ለሥራ አስፈጻሚ አባልነት በሚደረግ ምርጫ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን መገደቡን በመጥቀስ ማስተካከያ እንዲደረግ የጠየቁት አቶ ዮሐንስ፣ በዚህ ረገድ በሌሎችም ፌደሬሽኖች በቅርቡ በኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር በዕጩነት በቀረቡት አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊት የውጭ አገር ዜጋ ናቸው በሚል ክርክር መፍጠሩን ጭምር ያስታውሳሉ፡፡ ለእነዚህ ችግሮች የስፖርት መተዳደሪያ ደንቦች ከአገሪቱ መደበኛ ሕጎችና አዋጆች ጋር ተጣጥመው አለመቀረፃቸው  መሆኑን ጭምር ለፌዴሬሽኑ ባስገቡት የሕገ መንግሥታዊነት ጥያቄ አካተዋል፡፡

የፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ ከዚህም በተጨማሪ በአንቀጽ 58 መሠረት ተዘጋጅቶ የወጣው ደንብና መመርያ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) እና በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ደንቦችና መመሪያዎች ያልተጠቀሱ ቢኖሩና ከአገሪቱ መደበኛ ሕጎች ጋር የሚቃረኑ ልዩ ድንጋጌዎች እንኳ ቢያጋጥሙ፣ የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጉዳዩን አጣርቶ ስህተቱን በማስተካከል ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን እንደሚደነግግ የሚናገሩት አቶ ዮሐንስ፣ ይህንኑ በግልባጭ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለዳያስፖራ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት፣ ለወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴርና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳውቀዋል፡፡

 

Standard (Image)

የገናናው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ሥርዓተ ቀብር በሀገራዊ ክብር ዛሬ ይፈጸማል

$
0
0

የኦሊምፒክና የዓለም ዋንጫ በ5,000 ሜትርና በ10,000 ሜትር ሻምፒዮን የነበረው የገናናው አትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ሥርዓተ ቀብር ዛሬ እሑድ ታኅሣሥ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ ስምንት ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል፡፡

በመተንፈሻ አካል ችግር ምክንያት ሕክምናውን ሲከታተልበት በነበረው ካናዳ ታኅሣሥ 13 ቀን በቶሮንቶ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 3 ሰዓት 05 ደቂቃ ያረፈው ሻምበል ምሩፅ፣ አስክሬን አዲስ አበባ የሚደርሰው፣ በዛሬው ዕለት ከጧቱ አንድ ሰዓት ከሩብ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

የኮሚቴው ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት በቀለ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በታላቅ ሀገራዊ ክብር በሀገር መከላከያ ሠራዊት የክብር ዘብ ታጅቦ ሥርዓተ ቀብሩ ይፈጸማል፡፡ በቤተሰቡና በከፍተኛ የመንግሥት ሹማምንት አቀባበል ከተደረገ በኋላ አስክሬኑ ቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ቆይታ ያደርጋል፡፡ ስንብትና በክብር መዝገብ ላይ አስተያየት የሚሰጥበት ሥነ ሥርዓት ከተከናወነም በኋላ በታላቅ ወታደራዊ አጀብ በቦሌ ዋናው መስመር፣ በዳግማዊ ምኒልክ ጎዳና ከመስቀል አደባባይ ሽኝት በኋላ ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሲያመራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አካባቢ እንደደረሰ በማርሽ ባንድ መሪነት በሐዘን ዜማ ታጅቦ ከማረፊያው ይደርሳል፡፡

በቤተ ክርስቲያኒቱ ከሚኖረው ሃይማኖታዊ ሥርዓት ባሻገር፣ የአገሪቱ ርእሰ መንግሥት፣ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መልዕክቶች እንደሚተላለፉ ታውቋል፡፡

ለገድለኛው (ሌጀንድ) ኢትዮጵያዊ ሯጭ ምሩፅ ይፍጠር፣ ባረፈበት የካናዳዋ ቶሮንቶ ከተማ፣ ማክሰኞ ታኅሣሥ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በዚያው በምትገኘው ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ፍትሐት መደረጉ ይታወሳል፡፡

 ‹‹ይፍጠር ዘሺፍተር›› (ማርሽ ቀያሪው ምሩፅ ይፍጠር)፣ ‹‹ይፍጠር ዘማስተር›› (የሩጫ ጌታው ምሩፅ ይፍጠር) በመባል የዐቢይ አድናቆት ባለቤት የነበረው ምሩፅ ይፍጠር  በ1972 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1980) በሞስኮ ኦሊምፒክ ሁለት ወርቆችን በ10,000 ሜትርና በ5,000 ሜትር፣ በ1964 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1972) በሙኒክ ኦሊምፒክ በ10,000 ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ ያሸነፈ ሲሆን፤ አህጉሮች በሚወዳደሩበትና በ1969 እና በ1971 ዓ.ም. በተከታታይ በተካሄዱት የዱዞልዶርፍና የሞንትሪያል የዓለም አትሌቲክስ ዋንጫ ምሩፅ ይፍጠር አራት ወርቆችን በ10,000 ሜትርና  በ5,000 ሜትር ለአፍሪካ ማስገኘቱ ይታወቃል፡፡

ገድለኛው ምሩፅ በዐሥራ ስድስት ዓመታት የሩጫ ሕይወቱ፣ ከመካከለኛ ርቀት ማለትም ከ1,500 ሜትር እስከ ረዥም ርቀት (5,000 እና 10,000 ሜትር)፣ እንዲሁም ግማሽ ማራቶንን ጨምሮ ባሉት ርቀቶች በመወዳደርና ከ250 በላይ በመወዳደር በአንደኛነት ማጠናቀቁ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የኦሊምፒክ ሻምፒዮኑ ምሩፅ ሥርዓተ ቀብሩን በክብር ለማስፈጸም ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ከብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ከቤተሰቡ የተወጣጡ አባላት ያሉት ኮሚቴ እየሠራ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ከአባቱ አቶ ይፍጠር ተክለሃይማኖትና ከእናቱ ወ/ሮ ለተገብርኤል ገብረአረጋዊ በ1937 ዓ.ም. በትግራይ፣ ዓዲግራት የተወለደውና በ72 ዓመቱ ያረፈው ምሩፅ ይፍጠር የሰባት ልጆች አባት ነበር፡፡

 

 

Standard (Image)

አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ አሠልጣኞችን ይፋ አደረገ

$
0
0

 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በከፊል በቀድሞ አትሌቶች መመራት ከጀመረ በኋላ የመጀመሪያውን የብሔራዊ አሠልጣኞች ምርጫ ይፋ አደረገ፡፡ የቀድሞ የረዥም ርቀት ዋና አሠልጣኝ የነበሩት ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ የረዥም ርቀት የዋና አሠልጣኝ ኃላፊነት  አግኝተዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ በምርጫው ቅሬታ ያላቸው ካሉ የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜም አስቀምጧል፡፡

በዚሁ መሠረት በቀድሞ የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አካላት የወጣት ብሔራዊ ቡድኑ የረዥም ርቀት ዋና አሠልጣኝ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ሳይቀበሉ የቀሩት ዶ/ር ይልማ በርታ፣ በአዲሱ ሥራ አስፈጻሚ ምርጫ የፕሮጀክቶች፣ የማዕከላት፣ የክለቦች እንዲሁም የብሔራዊ ቡድኖችና የማናጀሮች ሥልጠና ዋና አስተባባሪ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡ የቀድሞ ማራቶን አሠልጣኝ አቶ መላኩ ደረሰ ደግሞ የማዕከላት፣ ፕሮጀክቶችና አካዴሚ ሥልጠና ክትትል ኃላፊ አድርጎ ሾሟቸዋል፡፡

ለበርካታ ዓመታት ከብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ምርጫና ምደባ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት ሲፈጠርበት የሚደመጠው የረዥም ርቀት ዋና አሠልጣኝ ቦታ ነው፡፡ በሻለቃ ኃይሌ የሚመራው አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በዚሁ ውዝግብ  ምክንያት ከፌዴሬሽኑ የብሔራዊ አሠልጣኝነት ርቀው የቆዩት ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ  የርቀቱ ዋና አሠልጣኝ እንዲሆኑ መርጧቸዋል፡፡ በርቀቱ የቀድሞ ዋና አሠልጣኝ የነበሩት ሱፐርኢንቴንደት ሁሴን ሽቦ የምክትል ዋና አሠልጣኝነቱ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል፡፡ በአሠልጣኝነት ደግሞ ኮማንደር ቶሌራ ዲንቃ፣ አቶ ባሕሩ ሚኮ፣ ወ/ት ሰናይት ኃይሌ፣ አቶ በሪሁን ተስፋዬና ኮማንደር አበበ መኰንን ተመድበዋል፡፡

በዚሁ ርቀት የታዳጊ ወጣት ብሔራዊ ቡድን የዋና አሠልጣኝነቱ ኃላፊነት ለአቶ ንጋቱ ወርቁ ሲሰጥ፣ አቶ ካሱ ዓለማየሁ ምክትል ዋና አሠልጣኝ ሆነዋል፡፡ በአሠልጣኝነት ኢ/ር ግርማ ፈዬ፣ አቶ ይበልጣል መርሻ፣ አቶ ብርሃኑ መኰንንና ወ/ሮ ንጋቷ ወልዴ ሆነዋል፡፡

በ3,000 ሜትር መሰናልክ አቶ ተሾመ ከበደ ዋና አሠልጣኝ ሲሆኑ፣ አቶ ብዙነህ ያኢ፣ አቶ ብዙአየሁ ታረቀኝ፣ ሻምበል ዮሐንስ መሐመድና ሻምበል እሸቱ ቱራ በአሠልጣኝነት ተመርጠዋል፡፡

ዕርምጃ በዋና አሠልጣኝነት ሻለቃ ባዩ አሰፋ ሲመረጡ፣ ወ/ት አምሳል ያዕቆብ በምክትልነት ተመርጠዋል፡፡ ለአጭር ርቀት ደግሞ አቶ አብዱልአዚዝ ሁሴን ዋና አሠልጣኝ ሲሆኑ፣ ሻምበል ሙሉጌታ መለሰ፣ አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ፣ ወ/ት ንፁህ ወንድሜነህ፣ ወ/ት ብርቱካን ቀፀላና አቶ ገነት ባዲ በአሠልጣኝነት ተመርጠዋል፡፡

ለመካከለኛ ርቀት ዋናው ቡድን አቶ ንጉሤ ጌቻሞ ዋና፣ አቶ ዳዊት ጥሩነህ ለምክልት ዋና አሠልጣኝ ሲመረጡ፣ በአሠልጣኝነት ወ/ት ዘውዴ ኃይለ ማርያምና አቶ ሀብታሙ ግርማ ሆነዋል፡፡ ለወጣቱ ቡድን አቶ ስንታየሁ ካሳሁን ዋና፣ አቶ አብርሃ ኃይለ ማርያም ምክትል ዋና አሠልጣኝ ሲሆኑ፣ አቶ ፈጠነ ታደሰና አቶ ንጉሤ ደምሴ አሠልጣኝ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ለውርወራ አቶ ቤተሳይዳ ተሾመ ዋና ሲሆኑ ወ/ት ዝናሽ ታከለ በምክትል አሠልጣኝነት ተመርጠዋል፡፡ ለዝላይ አቶ ለማ ደበሌ ዋና ሲሆኑ፣ አቶ ጋሻው በዛለማ በምክትል አሠልጣኝነት ተመድበዋል፡፡

 

Standard (Image)

​ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዶፒንግ በሚገኝባቸው አትሌቶች ላይ የዕድሜ ልክ ዕገዳ እንደሚጥል አስታወቀ

$
0
0

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዶፒንግ (አበረታች ንጥረ ነገር) በሚገኝባቸው አትሌቶች ላይ የዕድሜ ልክ ዕገዳ እንደሚጥል አስታወቀ፡፡ ከፌዴሬሽኑ ዕውቅና ውጭ በየትኛውም አገር ተወዳድረው የችግሩ ሰለባ በሚሆኑ አትሌቶች አገሪቱ ተጠያቂ እንደማትሆን ጭምር ገልጿል፡፡

በቅርቡ ወደ ኃላፊነት የመጣው የብሔራዊ ፌደሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ረቡዕ ታኅሣሥ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በብሔራዊ ሆቴል በሰጠው መግለጫ፣ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) የፀረ አበረታች ኤጀንሲ (ዋዳ) ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአምስት የዓለም አገሮች የሰጠውን ማስጠንቀቂያ መነሻ በማድረግ የመፍትሔ አማራጭ ያለውን በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ የዓለም አቀፍ ፀረ አበረታች ንጥረ ነገሮች ኤጀንሲ (ዋዳ) በስድስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ላይ ምርመራ እንዲደረግባቸው ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

ይህንኑ የዓለም አቀፉ የፀረ አበረታች ንጥረ ነገሮች ኤጀንሲ (ዋዳ) ያስተላለፈውን ትዕዛዝ መነሻ በማድረግ፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በተለይ በአበረታች ንጥረ ነገሮች በሚጠረጠሩ አትሌቶች ላይ በሚወስዳቸው አምስት የውሳኔ ሐሳቦች ላይ ማብራሪያም ሰጥቷል፡፡

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በተገኘበት በተሰጠው ማብራሪያ መሠረት፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ዶፒንግ በሚገኝባቸው አትሌቶች ምንም ዓይነት ድርድርም ሆነ ይቅርታ አይኖረውም፡፡ ለእውነተኛና ንፁህ አትሌቶች መብትም በማንኛውም ሁኔታ እስከ መጨረሻው እንደሚቆም፣ ይህ የአቋም መግለጫ በፌዴሬሽኑ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከአበረታች ንጥረ ነገሮችና ድርጊቶች ጋር ተያይዞ ከሚነሱ አትሌቶች፣ ማናጀሮችና አሠልጣኞች ጋር አብሮ እንደማይሠራም አስታውቋል፡፡

አዲሱን የፀረ አበረታች እንቅስቃሴን ትኩረት በምርመራ ላይ በማተኮር፣ ከብሔራዊ የፀረ ዶፒንግ ጽሕፈት ቤት ጋር አብሮ በመቀናጀት እ.ኤ.አ. ከ2017 ጀምሮ 200 ናሙናዎችን በመውሰድ ምርመራ ለማሠራት ስለማቀዱም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ በዚህ መሠረት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽንና ከዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) የዕገዳ ቅጣት በተጨማሪ የአገሪቱ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 526 መሠረት በማድረግ ከአበረታች ንጥረ ነገሮች ጋር ተያይዞ ወንጀል የሠራ ማንኛውም አካል በኢትዮጵያ ሕግ ተጠያቂ እንደሚሆንም ፌዴሬሽኑ ገልጿል፡፡

በመግለጫው እንደተገለጸው ከሆነ፣ አንቀጽ 526 ዶፒንግን አስመልክቶ ሲያብራራ ማንም ሰው በተፈጥሮና በሥልጠና የተገኘው የአካል ብቃት በጊዜያዊ መልክ በይበልጥ እንዲጨምር በማድረግ በስፖርቱ ውድድር ጊዜ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ የበላይነት ለማግኘት የሚረዱ በሕግ የተከለከሉና ጎጂ የሆኑ ሰው ሠራሽ ነገሮችን ያመረተ፣ ወደ አገር ውስጥ ያስገባ፣ በባለሙያነት ያዘዘና ያከፋፈለ፣ እንዲሁም ቀደም ሲል በተጠቀሱት ነገሮች በሕገወጥ መንገድ የተጠቀመ፣ ወይም ሌላ ሰው እንዲጠቀምባቸው ያደረገ እንደሆነ በቀላል እስራት ይቀጣል፡፡ መቀጮው ወይም ድርጊቱ ከባድ ጉዳት ባስከተለ ጊዜ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ማስቀመጡን በዝርዝር አስረድቷል፡፡

ፌዴሬሽኑ በተጨማሪም ከዚሁ ከአበረታች ንጥረ ነገሮች ጋር ተያይዞ በአይኤኤኤፍ አራት ዓመት ዕገዳ ከተጣለበትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባል ከሆነ  እስከመጨረሻው ዕገዳ እንደሚጣልበት ጨምሮ አስታውቋል፡፡

 

Standard (Image)

የቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ጉባኤ የደቡብ ክልልን ቅሬታ ሳይቀበለው ቀረ

$
0
0

የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ማክሰኞ ታኅሣሥ 25 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ከፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳነት ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ የውክልና ደብዳቤ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮና ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን የቀረበውን ቅሬታ ሳይቀበለው ቀረ፡፡

ጉባኤውም ዶ/ር አሸብር ለምርጫ የቀረቡበት ሒደት ትክክለኛ መሆኑን ተቀብሎ፣ አዲስ ምርጫ ማድረግ እንደማይጠበቅበት ቅሬታ አቅራቢው ክልል ጨምሮ በሙሉ ድምፅ ውሳኔውን አሳልፏል፡፡ የደቡብ ክልል ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ክልሉ ለዶ/ር አሸብር ውክልና የተሰጠበት አግባብ ተገቢ አይደለም ከሚለው በስተቀር ለምን ተመረጡ? የሚል አቋም የሌለው መሆኑን ለጉባኤው ገልጿል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ኅዳር 29 ቀን 2009 ዓ.ም. በዚሁ በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ከደቡብ ክልል ውክልና ያገኙት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስን ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ በጉባኤው የተሳተፉት የደቡብ ክልል ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ደምሴ ኤርጀቦ ለዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ድምፅ የሰጡበት አግባብ እንደነበርም ታውቋል፡፡

የብሔራዊ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በተጠናቀቀ ከቀናት በኋላ ግን የደቡብ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከክልሉ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ለዚህ ኃላፊነት ክልሉ ውክልና እንዳልሰጣቸው በመግለጽ ጉዳዩን ለወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴርና ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በማሳወቅ ምርጫው እንደገና የሚደረግበት አግባብ እንዲፈጠር መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡

ምርጫው በተደረገበት ዕለት የክልሉ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንትና በክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአስተባባሪነት ሕጋዊ ደብዳቤ የተሰጣቸው አቶ ታምራት ታዬ ለምርጫው ዕውቅና እንዴት ሊሰጡ ቻሉ? የሚለው ሲያከራክር ከቆየ በኋላ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ እንደገና በጠራው ጉባኤ የክልሉ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ውስጣዊ አሠራሩን በመፈተሽ ራሱን መገምገም ሲገባው ቅሬታ ያቀረበበት መንገድ ትክክል አለመሆኑን በመጥቀስ ጉባኤው ክልሉን ተጠያቂ አድርጓል፡፡

የክልሉ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ደምሴ በበኩላቸው ከክልሉ ወጣቶችና ስፖርት የአስተባባሪነት ኃላፊነት ከተሰጠው አቶ ታምራት ታዬ ጋር ውክልናን በሚመለከት እንዳልተነጋገሩ፣ የተሰጠው ውክልናም እንዴትና በምን አግባብ እንደተሰጠ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተከራክረዋል፡፡ አቶ ታምራት በበኩላቸው፣ በእያንዳንዱ ጉዳይ በጋራ ተነጋግረው የወሰኑት ሆኖ ሳለ ጥያቄ ሲቀርብ ‹‹መካካድ›› ለምን ሊፈጠር እንደቻለ ለጉባኤው አስረድተዋል፡፡

የክልሉን ኃላፊዎች በጉዳዩ ያቀረቡትን ክርክር ያደመጠው ጉባኤው ባለአምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ጉባኤውን አጠናቋል፡፡ በአቋም መግለጫው ከተጠቀሱት መካከል የመጀመርያው ኅዳር 29 ቀን 2009 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ አካሂዶ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ የደቡብ ክልል ባነሳው ቅሬታ ላይ ክልሉ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የእጩነት ድጋፍ አልሰጠሁም ማለቱን ተከትሎ በተነሳው ቅሬታ ጉባኤው ዕጩው በክልሉ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን አስተባባሪ ፊርማና በክልሉ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ተረጋግጦ የቀረቡ መሆኑ፣ የደቡብ ክልል ማኅተሙ ሕጋዊ እንዳልሆነም ጉባኤው አስምሮበታል፡፡

የአቋም መግለጫው ሲቀጥል፣ ዕጩውን ያቀረበው የክልሉ ቅርጫት ኳስ አስተባባሪ ሕጋዊ መሆናቸው፣ የሥራ መደባቸው በተገቢው አካል ተረጋግጦ የቀረቡ መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ የደቡብ ክልል ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ማኅተሙ ትክክለኛ አይደለም ብሎ ላቀረበው በተደረገው ማጣራት መሠረት፣ የደቡብ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለተለያዩ ተቋማት 18 ማኅተሞች እንዲታተሙ በጠየቀው መሠረት ታትሟል፡፡ የደቡብ ክልል ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን የሚለው የእንግሊዝኛው ትርጉም ስህተት እንዳለው፣ ትክክለኛ ተብሎ ለክልሉ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት የቀረበው ማኅተም እንደዚሁ የኅትመት ስህተት እንዳለው አይተን አቻችለን አልፈናል፡፡ አቶ ታምራት ታዬም የደቡብ ክልል ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን አስተባባሪ መሆናቸውንም አረጋግጠናል፡፡ በመሆኑም የደቡብ ክልል ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን የውስጥ ችግሩን በራሱ እንዲፈታና ብሔራዊ ፌዴሬሽኑን እንዲያግዝ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የቀረበው ደግሞ፣ በዚሁ ምርጫ ላይ ዕጩዎች ከትግራይ፣ ከኦሮሚያና ከደቡብ ክልሎች ተወክለው በሁሉም ክልሎችና ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽኖች እንዲሁም ማኅበራት ዶ/ር አሸብር በሙሉ ድምፅ መመረጣቸው፣ ዕጩው ካቀረቧቸው የደቡብ ክልል ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን በተጨማሪ በሌላ አንድ ክልል ዕጩ ሆነው መቅረባቸውን አረጋግጠናል፡፡ ስለሆነም ድጋሚ ምርጫ ላለማካሄድ መግባባት ላይ ተደርሷል የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

Standard (Image)

የረዥም ርቀት ሩጫ ጀግናው ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ሥርዓተ ቀብር በወታደራዊ ሥርዓት ተፈፀመ

$
0
0

- ለክብሩ ዘጠኝ ጊዜ ተተኩሷል

በኦሊምፒክ፣ በሉላዊና በአህጉራዊ የአትሌቲክስ መድረኮች በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ ተደራራቢ ድሎቹ ነግሦ የነበረው ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ሥርዓተ ቀብር፣ እሑድ ታኅሣሥ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡

በሞስኮ ኦሊምፒክና በሌሎች መድረኮች በ5,000 ሜትርና በ10,000 ሜትር ሩጫ ከአሯሯጥ ስልቱና ከአጨራረስ ስኬቱ በመነሣት ‹‹ይፍተር ዘሺፍተር››- ማርሽ ቀያሪው ይፍጠር፣ ‹‹ይፍተር ዘማስተር››- የሩጫው ጌታ ይፍጠር- የሚሉ ቅፅል ስሞችን በዓለም ዙርያ የተጎናፀፈው የአየር ኃይል ሻምበል ምሩፅ፣ ሥርዓተ ቀብሩ እሑድ በስምንት ሰዓት በክብር ዘብና በማርሽ ባንድ ሐዘናዊ ቃና ታጅቦ ከመፈጸሙም ባሻገር፣ ግብዓተ መሬቱ ሲፈጸም ለክብሩ ዘጠኝ ጊዜ የተኩስ ድምፅ ተሰምቷል፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ ከአገር ቤትና ከካናዳ የመጡ ቤተሰቦችና ዘመዶች፣ ወዳጆችና የአሁንና የቀድሞ ሚኒስትሮች፣ የአሁንና የቀድሞ ጄኔራል መኰንኖች፣ ዲፕሎማቶች፣ ልዑላን ቤተሰቦችና አድናቂዎች በተገኙበት ሥርዓተ ቀብር ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የምሩፅን ሀገራዊ ውለታ ያስታወሰ የሐዘን መግለጫ መልእክት በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ርስቱ ይርዳው አማካይነት ተነቧል፡፡ ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴም ባደረገው ንግግር ምሩፅ የብዙዎች አርአያ እንደነበረ አስታውሷል፡፡

በካናዳ ቶሮንቶ ሐሙስ ታኅሣሥ 13 ቀን 2009 ዓ.ም. ያረፈው ሻምበል ምሩፅ አስክሬን አዲስ አበባ የደረሰው እሑድ ማለዳ ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከከፍተኛ ሹማምንት፣ ከስፖርት ማኅበረሰቡና ከቤተሰቡ ጋር በመሆን ተቀብለውታል፡፡ አስክሬኑ ከአውሮፕላን እንደወረደ የክብር ዘብ አጅቦታል፡፡

 እስከ ረፋዱ አምስት ሰዓት በቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ቆይታ ካደረገ በኋላ፣ በዳግማዊ ምኒልክ ጎዳና በመስቀል አደባባይ በኩል ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በማርሽ ባንድና በክብር ዘብ ዝግታ ጉዞ ሲያደርግ በየመንገዱ የነበሩ እግረኞችና ባለተሸከርካሪዎች ሐዘናቸውን ሲገልፁ ታይተዋል፡፡

በቤተ ክርስቲያኒቱ እንደደረሰም ጸሎተ ፍትሐቱ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ መሪነት የተከናወነ ሲሆን በካናዳ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ ዳግማዊ ተገኝተዋል፡፡

‹‹ይፍጠር ዘማስተር›› - ይፍጠር የሩጫው ጌታ

መስከረም 1961 ዓ.ም. (ሴምተምበር 1968) አበበ ቢቂላና ማሞ ወልዴን የያዘው በሜክሲኮ ኦሊምፒክ የሚሳተፈው ብሔራዊ ቡድን፣ የመጨረሻ ጉዞውን ወደ ሜክሲኮ ሲቲ ከማድረጉ በፊት ለልምምድ ቆይታ ያደረገው የኤርትራ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ በነበረችው አስመራ ነበር፡፡ ቡድኑ በንግሥተ ሳባ ስታዲየም ልምምድ ሲያደርግ ምሩፅ ይፍጠር የወደፊት ሕይወቱ በር ከፋች አጋጣሚ ፈጠረለት፡፡ በልምምድ ሩጫ ውድድርም ከነማሞ ወልዴ ጋር ተወዳድሮ ለውጤት ባይበቃም አሯሯጡንና አቅሙን ያስተዋሉት ዋና አሠልጣኝ ንጉሤ ሮባ በአየር ኃይል ስፖርት መምሪያ እንዲያዝና ልምምድ እንዲያደርግ አደረጉ፡፡ ቅጥሩንም ፈጸመ፡፡ ለ17 ዓመታት በአየር ኃይል ሲያገለግል እስከ ሻምበልነት ደርሷል፡፡ ከ1978 በኋላም ወደ ስፖርት ኮሚሽን ተዘዋውሯል፡፡

በአዲስ አበባው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስታዲየም፣ ንብ የሚባለውን የአየር ኃይል ስፖርት ክለብን እየወከለ በብሔራዊ ሻምፒዮናና በጦር ኃይሎች ውድድር ባለድል መሆን የጀመረው ምሩፅ፣ ካገኛቸው ሽልማቶች በተጨማሪ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የእጅ ሰዓት መሸለሙ ይታወቃል፡፡

ምሩፅ የመጀመሪያው ኢንተርናሽናል ውድድሩ በ1962 ዓ.ም. በምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታንዛኒያ ውስጥ በ1,500 ሜትር ከኦሊምፒክ ባለወርቁ ኬፕቾግ ኬይኖ ጋር ተወዳድሮ ሦስተኛ የወጣበት ውድድሩ ነበር፡፡ በ1963 ዓ.ም. በአሜሪካ በተካሄደው የአፍሮ አሜሪካን ውድድር በ10 ሺሕ ወርቅ፣ በ5 ሺሕ ሜትር ብር ሜዳሊያ በማግኘት ድሉን አሐዱ ብሎ ጀምሯል፡፡

በ1965 ዓ.ም. በሌጎስ (ናይጄሪያ) በተካሄደው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች በ10 ሺሕ ወርቅ በ5 ሺሕ ብር አሸንፏል፡፡ በዚያው ዓመት ከሁሉም የስፖርት ዓይነቶች ከተውጣጡት መካከል የኢትዮጵያ ስፖርት ኮከብ አትሌት ተብሎም ተመርጧል፡፡

የመጀመሪያው የኦሊምፒክ መድረኩ በሆነው 20ኛው ኦሊምፒያድ በሙኒክ ሲካሄድ ምሩፅ በ5 ሺሕና በ10 ሺሕ ሜትር ለመወዳደር ነበር ወደ ሥፍራው ያመራው፡፡ በ10 ሺሕ ሜትር በማጣሪያው አንደኛ ወጥቶ በፍጻሜው ሦስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያን ሲያገኝ፣ በ5 ሺሕ ሜትር ማጣሪያ ‹‹በአሠልጣኞቹ ችግር›› ምክንያት በጊዜ ባለመድረሱ የተነሳ ሳይወዳደር በመቅረቱ ሌላ ሜዳሊያ የማግኘት ዕድሉ ተጨናግፎበታል፡፡

በ1968 ዓ.ም. በሞንትሪያል (ካናዳ) በተካሄደው 21ኛው ኦሊምፒያድ ያለ ጥርጥር በ5,000 እና በ10,000 ሜትር ሁለት ወርቅ ያገኛል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ስፖርታዊ ግንኙነት የነበራት ኒውዚላንድ ከሞንትሪያል ኦሊምፒክ ባለመታገዷ ምክንያት አፍሪካውያን አንካፈልም በማለታቸው ሳይወዳደር ተመለሰ፡፡ በሙኒክ ኦሊምፒክ ምሩፅን ያሸነፈው ፊንላንዳዊው ላሲ ቨረን ዳግመኛ ድሉን ምሩፅ በሌለበት አጣጣመ፡፡

ምሩፅ የኦሊምፒክ ወርቅ ሕልሙን ያሳካው በ1972 ዓ.ም. ሞስኮ ባስተናገደችው 22ኛ ኦሊምፒያድ ሲሆን በሁለቱም ርቀቶች ወርቁን ያጠለቀው ፊንላንዳዊውን ላሲ ቨረንን ድል በመምታት ነበር፡፡

በሞስኮ ኦሊምፒክ ሲሮጥ ዕድሜው የገፋው (በፓስፖርት ዕድሜው 36 ዓመቱ በተለያዩ ሚዲያዎች እስከ 42 የሚያደርሱት) ምሩፅ፣ በ1969 ዓ.ም. እና በ1971 ዓ.ም. በተካሄዱት የዓለም አትሌቲክስ ዋንጫዎች አፍሪካን በመወከል አራት ወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ ተወዳዳሪዎቹን በቀደመበት ርቀት ያህል በሞስኮ አልደገመውም፡፡ ዕድሜው ገፍቷልና፡፡

በሁለቱ የዓለም ዋንጫዎች፣ በ5,000 ሜትር ውድድሩ ሊያበቃ 500 ሜትር ሲቀር፣ በ10 ሺሕ 600 ሜትር ሲቀር ነበር ማርሽ ቀይሮ በማፈትለክ ያሸነፈው፡፡ በሞስኮ ኦሊምፒክ ግን በሁለቱ ርቀቶች እንደ ቅደም ተከተላቸው 200 ሜትርና 300 ሜትር ሲቀረው ነበር ማርሽ ቀይሮ ድል የመታው ምሩፅ፤ በ1971 ዓ.ም. በዓለም ዋንጫ አፍሪካን ወክሎ ለመካፈል የበቃውም የመጀመሪያው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዳካር (ሴኔጋል) ሲካሄድ ሁለት ወርቅ (በ5 ሺሕና 10 ሺሕ) በማግኘቱ ነበር፡፡

ምሩፅ 1971 ዓ.ም. ወርቃማ ዓመቱ ነበር፡፡ እጅግ የገነነበት ታላቅ ክብርንም የተቀዳጀበት፡፡ በዚያው ዓመት በቼኮዝሎቫኪያ በተዘጋጀው የዓለም ኮከብ አትሌቶች ምርጫ ከተመረጡት ዘጠኝ አትሌቶች አንዱ ምሩፅ ሲሆን፣ ‹‹የኮከቦች ኮከብ›› ተብሎ መመረጡና በተዘጋጀው የተሸላሚዎች መድረክ ከመሃል በከፍታ መቀመጡ ይታወሳል፡፡ የወርቅ ጫማም ተሸላሚ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት (የኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ) ሻምበል ምሩፅ በቅድመ ሞስኮ ኦሊምፒክ ባገኛቸው አህጉራዊና ኢንተርናሽናል ድሎች ኢትዮጵያን ለታላቅ ግርማ ሞገስ በማብቃት ለፈጸመው አኩሪ ተግባር አምስተኛው የአብዮት በዓል ሲከበር ‹‹የጥቁር ዓባይ ኒሻን››ን ከርዕሰ ብሔሩ ሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እጅ መቀበሉ ይታወሳል፡፡

በ800 ሜትር በ1,500 ሜትር መወዳደር የጀመረው ምሩፅ፣ 5 ሺሕና 10 ሺሕ መደበኛ ውድድሮቹ ቢሆኑም በጎዳና ላይ ሩጫዎችም ተደጋጋሚ ድሎች ማግኘቱ አይሳትም፡፡

በተለይ በተከታታይ ዓመታት ድል የተጎናፀፈበት የፖርቶ ሪኮ ግማሽ ማራቶን ውድድር ለዓለም ክብረ ወሰን የበቃበት ነበር፡፡ ጥር 29 ቀን 1969 ዓ.ም. በፖርቶ ሪኮ ኮዓሞ የ21 ኪሎ ሜትር (ግማሽ ማራቶን) ውድድር ምሩፅና መሐመድ ከድር ተከታትለው ሲያሸንፉ፣ ምሩፅ የገባበት 1 ሰዓት 02 ደቂቃ 57 ሰከንድ ያለም ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቦለታል፡፡

በ1972 በፖርቶ ሪኮ ግማሽ ማራቶን አሸንፎ እንደተመለሰ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫም ‹‹የማተኩረው በሞስኮ ኦሊምፒክ ስለሆነ በፖርቶ ሪኮው ድሌ አልኮራም›› ማለቱ አይዘነጋም፡፡

በሞስኮ ኦሊምፒክ ለሦስተኛ ጊዜ ድሉን ለማጣጣም ቋምጦ የነበረው ፊንላንዳዊ ላሲ ቬረን በሞስኮ አየሩ ጥሩ ከሆነ እንደሚያሸንፍ መናገሩን ተከትሎ ምሩፅ በሰጠው አፀፋ ‹‹ሐሩርም ይሁን በረዶ እኔ ከማሸነፍ የሚገታኝ አንዳች ኃይል የለም›› ማለቱ ልበ ሙሉነቱን ያሳየበት አጋጣሚ ነበር፡፡

የሞስኮ ኦሊምፒክ ድሉ ምሩፅን አስደናቂና ትንግርተኛ አትሌት ያደረገው፣ በዘመኑ ኦሊምፒክ እንዳሁኑ በቀጥታ የ10 ሺሕ ፍፃሜ ብቻ ሳይሆን ማጣሪያውን አልፎ በጥቅሉ 20 ሺሕ ሜትር መሮጡ፣ እንዲሁም በ5ሺሕ ለፍፃሜ ድሉ የበቃው ሁለት ማጣሪያዎቹን በድል በመወጣትና በጥቅሉ 15ሺሕ ሜትር በመሮጥ ነበር፡፡ 

ከሞስኮ ኦሊምፒክ ድሉ በኋላ ጥንታዊ ኦሊምፒክ በተመሠረተበት ግሪክ ለኦሊምፒያዊ ሽልማት ከተመረጡ አምስት አትሌቶች ቀዳሚ ሆኖ የኦሊምፒክ ሎሬት አክሊልን ከርዕሰ ብሔሩ የተቀበለው ምሩፅ ይፍጠር ነበር፡፡

በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ ‹‹አረንጓዴ ጎርፍ›› የተሰኘ መጠርያ ያተረፈው በ1973 ዓ.ም. የዓለም አገር አቋራጭ ውድድር በ12 ኪሎ ሜትር በተወዳደረውና በቡድን አንደኛ በወጣው ስብስብ ውስጥ አንዱ የነበረው ምሩፅ ይፍጠር ነበር፡፡ በ1974 እና በ1975 ዓ.ም. በተካሄዱት ተመሳሳይ ውድድሮችም ተሳትፏል፡፡ በሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክ በማራቶን ለመወዳደር አልሞ የነበረው ምሩፅ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሶቭየት ኅብረት አልካፈልም በማለቷ ‹‹አጋርነቱን›› ለመግለጽ አገሪቱ እንዳትሳተፍ በማድረጉ ሕልሙ እውን አልሆነለትም፡፡ ከ13 ዓመት በላይ ባስቆጠረው የኢንተርናሽናል ተወዳዳሪነቱ ምሩፅ 271 ጊዜ ድል ማድረጉ ይነገርለታል፡፡

በዓለም ገናና ለሆነው ኃይሌ ገብረሥላሴን ጨምሮ ለኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለሞሮኮው ሰዒድ አዊታና ሌሎች አፍሪካውያን አርአያ የሆነው ምሩፅ፣ ኢንተርናሽናል አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር በ1973 ዓ.ም. በምዕራብ ጀርመን ባደን ባደን ጉባኤውን ሲያካሂድ፣ የዓለም አትሌቶችን ከወከሉ ሁለት አትሌቶች አንዱ ርሱ ነበር፡፡ ሁለተኛው ተወካይ እንግሊዛዊው ያሁኑ የኢንተርናሽናል አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር ፕሬዚዳንት የያኔው የሞስኮ ኦሊምፒክ የ1,500 ሜትር ባለድል ሰባስቲያን ኮ ነበር፡፡

ከአባቱ አቶ ይፍጠር ተክለሃይማኖትና ከእናቱ ወ/ሮ ለተገብርኤል ገብረአረጋዊ ጥቅምት 5 ቀን 1936 ዓ.ም. በቀድሞ አጠራሩ በትግራይ  ጠቅላይ ግዛት፣ ዓጋመ አውራጃ፣ ዛላምበሳ ወረዳ እመበይቶ በተሰኘ ቦታ  የተወለደውና በ72 ዓመቱ ያረፈው ምሩፅ ይፍጠር የስምንት ልጆች አባት ነበር፡፡

በመኖሪያ ቤቱ በተዘጋጀው የሐዘን መግለጫ መዝገብ ላይ በላይ አቶ በቀለ ወያ እንዲህ ገጠሙ፡፡

‹‹በታሪክ መንገድ - ማርሽ ቀያሪ

በታሪክ ሀገር - ታሪክ ፈጣሪ

በሠራው ሥራ - ህያው ነውና

ሞተ አይባልም - ሲያርፍ አንድ ጀግና፡፡››

 

Standard (Image)
Viewing all 339 articles
Browse latest View live